![](https://cdn.al-ain.com/images/2021/9/30/245-114134-dr-yilekal-1_700x400.jpg)
የክልሉ ምከር ቤት አዲስ አፈ ጉባዔ እና ምክትል አፈ ጉባዔም ሰይሟል
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስረታ በዛሬው እለት እየተካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ አለሙ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ አቶ አማረ ሰጤ ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል።
በተጨማሪም የአማራ ክልል ምከር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።
ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ኃላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል።