የአማራ ክልል መንግስት ግጭቱን የጀመሩት “የክልሉን ሕዝብና መንግሥት መረጋጋት የማይሹ” ሃይሎች ናቸው አለ
በሁለቱ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢዎች በተደጋጋሚ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶች ደርሰዋል
የክልሉ መንግስት “የተፈጸመው ጥቃት የጥፋት ኃይሎች በክልሉ ሕዝብ ላይ የደቀኑት የጥፋት መጠን ለከት አልባነት ያረጋግጣል” ብሏል
የአማራ ክልል መንግስት ዛሬ ባውጣው መግለጫ ከሰሞኑ አማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት የፈጠሩት “የክልሉን መረጋጋት የማይሹ የጥፋት አምባሳደሮች ናቸው” ብሏል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት መትፋቱን እና ንብረት መውደሙን በትንናንትነው እለት ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸው ነበር፡፡
የክልሉ መንግስትም በደረሰው ግጭት በልዩ ኃይል ፖሊስ እና በፌደራል ፖሊስ ላይ ጥቃት መድረሱን አስታውቋል፡፡
“ከድህረ ጦርነት በኋላ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት በተረጋጋ ሁኔታ ላይ መገኘትን የማይሹ የቀውስ አምባሳደሮች የክልሉን ሕዝብና መንግሥት በግጭት አዙሪት ውስጥ መልሶ ለመዝፈቅ ከመቅበዝበዝ፤ በንጹሃን ዜጎችና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት ከመሰንዘር አልቦዘኑም፡፡” ብላል የክልሉ መንግስት፡፡
የክልሉ መንግስት “የተፈጸመው ጥቃት የጥፋት ኃይሎች በክልሉ ሕዝብ ላይ የደቀኑት የጥፋት መጠን ለከት አልባነት ያረጋግጣል” ብሏል፡፡
ክልሉ እንገለጸው የጥፋት ሃይሎች ያላቸው አካላት ከጸጥታ ኃይሎች በተጨማሪ በሁለቱ ዞን “በሆኑ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ እያደረሱም ይገኛል።”
መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም እና ጥፋተኖችን ለማያዝ ተሰማራተው ስራ እያከናወኑ ነው ብሏል፡፡
መንግስት የጥፋት ሃይሎች በሚላቸው አካላት በሁለቱ ዞኖች አዋሳኝ አካባቢ በሚያደርሱት
ተደጋጋሚ ጥቃቶች ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳቶች ደርሰዋል፡፡