በ6 ወራት የህዝቡን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውል ወስኗል
የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤው የክልሉን ሰንደቅ ዓላማ ለመቀየር የቀረበውን አዋጅ አፀደቀ።
በቀጣይ 6 ወራት በጥናት ላይ ተመስርቶ የአማራ ህዝብን ታሪክና ስነ ልቦና የሚያንፀባርቅ ሰንደቅ ዓላማ ተዘጋጅቶ ጥቅም ላይ እንዲውልም ምክር ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።
ነባሩ ሰንደቅ ዓላማ አንድን ፓርቲ የሚወክል እንጂ የአማራ ህዝብን ስነ ልቦና የማያንፀባርቅ በመሆኑ በህዝቡ ተቀባይነት ማጣቱም በምክር ቤቱ ተገልጿል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 17ኛ መደበኛ ጉባኤ ከመጋቢት 2 2013 ጀምሮ በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጆችን እንዲሆም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።