ከሀይቁ ናሙናዎች ወደ ተለያዩ ላቦራቶሪዎች ተልከው ሀይቁን ወደ ሮዝነት የቀየረውን ምንክያት ጥናት እየተካሄደ ነው
ከሀይቁ ናሙናዎች ወደ ተለያዩ ላቦራቶሪዎች ተልከው ሀይቁን ወደ ሮዝነት የቀየረውን ምንክያት ጥናት እየተካሄደ ነው
በህንድ 50ሺ ዓመት እድሜ ያለው ሀይቅ ወደ ሮዝነት (ፒንክ)ተቀይሯል፤ባለሙያዎች ለምን እንደተከሰተ በትክክል ያወቁት ነገር እንደሌለ ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ሀይቁ ወደ ሮዝነት እንዲቀየር ያደረገው ምክንያት ምንድነው?
ይህ ጥያቄ ማሀራስትራ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ሎናር ሀይቅ በድንገት ቀለም ከቀየረ በኋላ በህንዳውያን አእምሮ እየተመላለሰ ያለ ጥያቄ ነበር፡፡
ባለሙያዎች ክስተቱ እየጨመረ ባለው የውሃው የጨው መጠን ወይም በአልጌ መፈጠር ወይንም በሁለቱም ምክንያት በኡታህ ትልቅ ጨዋማ ሀይቅ አካል ላይ ወይንም በአውስትራሊያው ሂለር ሐይቅ እንደተከሰተው አይነት ሊሆን እንደሚችል ያምናሉ፡፡
ጋጃናን ካራት የተባለ የአካባቢው የስነምህዳር ባለሙያ በተንቀሳቃሽ ምስል ባስተላለፈው መልእክት “እንዲህ አይነት ነገር ተከስቶ ያውቃል፤ነገርግን ይህን ያህል ታዋቂ አልነበረም፡፡”
“በዚህ አመት በተለይ የውሃው ጨዋማነት ጨምሯል፤የሀይቁ ውሃ መጠንና ጥልቀቱ ቀንሷል፡፡ የጨው መጠኑ መጨመሩ የተወሰነ ለውጥ እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል፡፡”
ካራት እንዳለው በሀይቁ ላይ ያለው ቀይ አልጌ ለውጡን አምጥቶት እንደሆነ በሚል ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡
ናሙናዎች ወደ ተለያዩ ላቦራቶሪዎች እየተላኩ ነው ያለው ካህራት ጥናቱን ሲጨርሱ ሀይቁን ወደ ቀይ የቀየረውን ምንክያት ይናገራሉ ብሏል፡፡
ሀይቁ ከሙባይ በ500 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ትልቅ የጎብኝዎች መዳረሻ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡