ተቋርጦ የነበረው የግድቡ ድርድር ደቡብ አፍሪካን፤አውሮፓ ህብረትና አሜሪካን በታዛቢነት በመሰየም እየተካሄ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል
ተቋርጦ የነበረው የግድቡ ድርድር ደቡብ አፍሪካን፤አውሮፓ ህብረትና አሜሪካን በታዛቢነት በመሰየም እየተካሄ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል
በግድቡ ዙሪያ የሶስትዮች ድርድር የጀመሩት ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን “የታዛቢዎቹ ሚና ምን ይሁን ” በሚለው ጉዳይ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን የኢትዮጵያ ውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሶስቱ ሀገራት መካከል በአሜሪካ ሲካሄድ በነበረው ድርድር ላይ አሜሪካና የአለም ባንክ በታዛቢነት ቢሰየሙም፣ ወደማደራደርና ወደ ድርድር ሰነድ አርቃቂነት ሚናቸው ተቀይሯል በማለት ኢትዮጵያ ማለመስማማቷ ነበር ድርድሩ ሳይቋጭ የቀረው፡፡
ኢትዮጵያ ድርድሩ እንዲቀጥል ከተስማማች በኃላ የሶስቱ ሀገራት የውኃ ሚኒስትሮች ሴኔ 2 ቀን 2012 ዓ.ም በበይነ-መረብ ቪዲዮ ኮንፈረንስ አካሂደዋል፡፡
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው በድርድሩ ስነስርአት፣በታዛቢዎች ገዳይና በድርድሩ ያልተቋጩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፤ተከታታይ ውይይቶችም ለማካሄድ ሀገራቱ ተስማምተዋል ብሏል፡፡
በድጋሚ በተጀመረው ድርድር ላይ ተደራዳሪዎቹ ሶስቱ ሀገራቱ የአውሮፓ ህብረት፣ደቡብ አፍሪካና አሜሪካ እንዲታዘቡ ስምምነት ላይ ቢደረስም ታዛቢዎቹ በሚኖራቸው ሚና ላይ አልተስማሙም፡፡
የሱዳኑ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ከትናንት በስትያ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያ፣አሜሪካ በግብጽ እና የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በሱዳን የተመረጡ ታዛቢዎች ናቸው ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ልዩነቶችን በድርድር ለመፍታት ሁሌም ዝግጁ ናት ያለው የኢትዮጵያ ውኃ መስኖና ኢነርጂ በመግለጫው “የሶስቱ ሀገራት ድርድር የግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ዓመታዊ አለቃቀቅ ላይ ብቻ የተወሰነ ይሆናል” ብሏል፡፡
ኢትዮጵያ ግድቡን የምትገነባው ልማትን ለማፋጠን መሆኑን በተደጋጋሚ ብትገልጽም በግብጽ በኩል ከናይል የማገኘው የውኃ መጠን ይቀንሳል የሚል ቅሬታ ስታነሳ ቆይታለች፡፡ ሱዳን በአንጻሩ የግድቡን መገንባት እንደማትቃወም ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
በመጭው ሀምሌ ወር የግድቡን ውሃ ሙሌት ለመጀመር ኢትዮጵያ እቅድ አውጥታ እየሰራች ሲሆን ሱዳንና ግብጽ ስምምነት ላይ ሳይረስ ሙሌቱ መጀመር የለበትም የሚል አቋም ይዘዋል፡፡