ባንድ ወቅት ነፍሱን ለማትረፍ ሲል የጀመረው ሲሚንቶ የእድሜ ልክ ምግቡ ሊሆን ችሏል
ሲሚንቶ የሚመገበው ሰው
ኢንዶኔዢያዊው ዳኤንግ ንጋሌ ሲሚንቶን መመገብ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ሲሚንቶን እንደ ምግብ ማጣፈጫነት የሚጠቀመው ይህ ግለሰብ እስካሁን ምግቡ እንደተስማማው ገልጿል።
ባንድ ወቅት ለስራ ወደ አንድ እቃዎች ማከማቻ ወይም መጋዝን ውስጥ ገብቶ በቀላሉ መውጣት አለመቻሉን ተከትሎ በዛው ራሱን በህይወት ለማቆየት ሲል ሲሚንቶን መመገብ መጀመሩንም ተናግሯል።
ከገባበት አስቸጋሪ ቦታ በሰዎች እርዳታ መውጣቱን የሚናገረው ይህ ሰው በዛው ሲሚንቶ ዋነኛ ምግቡ እንደሆነም ገልጿል።
እንደብአርቲ ዘገባ ከሆነ ህይወትን ለማትረፍ ሲባል ከሶስት ዓመት በፊት የተጀመረው ሲሚንቶን መመገብ የእድሜ ልክ ምግብ ሆኗል።
ሲሚንቶን እንደ በሶ በጥብጦ መጠጣት የሚወደው ምግብ ነው የተባለ ሲሆን እንደ ሙዝ እና ሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀልም እመገባለሁም ብሏል።
ግለሰቡ በመላው ኢንዴኔዢያ ታዋቂነትን እና አግራሞትን ያተረፈ ሲሆን ሲሚንቶ መመገቡን እንደሚቀጥልም አስታውቋል።