'አስርቱ ትዕዛዛት' የተጻፉበት ጥንታዊ ድንጋይ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሸጠ
አስርቱ የመጽሃፍ ቅዱስ ትዕዛዛት የተጻፉበት ጥንታዊ የደንጋይ 'ታብሌት' ባለፈው ረቡዕ እለት በተካሄደ ጨረታ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሸጡን ኤፒ ዘግቧል
ጨረታውን ያካሄደው ኩባንያ ሶዝቤይስ 52 ኪል ግራም የሚመዝነውን ጥርብ ማርብል ለእስራኤል አሳልፍ መስጠት የፈለገ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ገዝቶታል ብሏል
'አስርቱ ትዕዛዛት' የተጻፉበት ጥንታዊ ድንጋይ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሸጠ።
አስርቱ የመጽሃፍ ቅዱስ ትዕዛዛት የተጻፉበት ጥንታዊ የደንጋይ 'ታብሌት' ባለፈው ረቡዕ እለት በተካሄደ ጨረታ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ መሸጡን ኤፒ ዘግቧል።
ጨረታውን ያካሄደው ኩባንያ ሶዝቤይስ 52 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን ጥርብ ማርብል ለእስራኤል አሳልፍ መስጠት የፈለገ ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ገዝቶታል ብሏል። መቀመጫውን ኒው ዮርክ ያደረገው ማጫረቻ ቤት(ሶዝቤይስ) እንደገለጸው ለ10 ደቂቃ የቆየ ጠንካራ ፉክክር በታየበት ጨረታ የተገኘው የመጨረሻው ዋጋ ከጨረታው በፊት ከተገመተው አንድ ወይም ሁለት ሚሊዮን ዶላር የበለጠ ነው።
እንደ ሶዝቤይስ ከሆነ ይህ ድንጋይ እድሜው ከክርስቶስ ልደት በኋላ ከ300-800 አመት ሲሆን ትዕዛዛቱ የተጻፉት በቅደመ እብራይስጥ ቃላት መሆኑ ጥንታዊነቱን የሚያሳይ ነው።
ድንጋዩ የተገኘው በ1913 በደቡብ እስራኤል ጠረፍ ለባቡር መንገድ ቁፋሮ በሚደረግበት ወቅት ሲሆን መጀመሪያ ላይ ታሪካዊ ጠቀሜታው አልታወቀም ነበር።
ድንጋዩ "አለምአቀፍ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ልምዶችን በጥልቀት ቅርጽ ከሰጡት ጥንታዊ እምነቶች ጋር የሚያገናኝ ነው፤ ብርቅ የታሪክ ምስክር ሆኖም ያገለግላል " ብሏል ኩባንያው።
በድንጋዩ ላይ የተጻፉት ጹህፎች ከክርስቲያኖች እና አይሁዶች ልምዶች ጋር የሚመሳሰሉ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ስንኞች ቢሆኑም "የእግዘብሔርን ስም በከንቱ አትጥሩ" የሚለውን ሶስተኛውን ትዕዛዝ አላካተተም።
ሶዝቤይስ እንዳለው ጹሁፉ በገሪዝም ተራራ ማምለክን የሚመለከት አዲስ መመሪያ አካቷል።