ማሌዥያ ከ 10 አመት በፊት የደረሰበት ያልታወቀውን አውሮፕላን በድጋሚ መፈለግ ልትጀምር ነው
የአውሮፕላኑ መሰወር በአለም የበረራ ታሪክ እጅግ ግራአጋቢ ሆኖ ተመዝግቧል
የበረራ ቁጥሩ ኤምኤች 370 የሆነው የቦይንግ አውሮፕላን የተሰወረው በመጋቢት 2014 ከኩአላ ላምፑር ወደ ቤጂንግ 277 ሰዎችን ይዞ እየበረረ በነበረበት ወቅት ነው
ማሌዥያ ከ 10 አመታት በፊት የደረሰበት ያልታወቀውን ንብረትነቱ የማሌዥያ ኤየርላንስ የበረራ ቁጥሩ ኤምኤች 370 የሆነውን አውሮፕላን ፍለጋ ድጋሚ ልትጀምር መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
የአውሮፕላኑ መሰወር በአለም የበረራ ታሪክ እጅግ ግራአጋቢ ሆኖ ተመዝግቧል።
የበረራ ቁጥሩ ኤምኤች 370 የሆነው ቦይንግ 777 አውሮፕላን የተሰወረው በመጋቢት 2014 ከኩአላ ላምፑር ወደ ቤጂንግ 277 ሰዎችን ይዞ እየበረረ በነበረበት ወቅት ነው።
የሀገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስትር አንቶኒ ሎክ ኦሽን ኢንፊኒቲ ከተባለው የአሰሳ ኩባንያ በደቡባዊ ህንድ ውቅያኖስ ፍለጋ ለመድረግ ሀሳብ መቅረቡን ተናግረዋል። ይህ ኩባንያ ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደውን እና በ2018 ያበቃውን የዚህን አውሮፕላን ፍለጋ ያካሄደ ነው።
የአውሮፕላኑ ስብርባሪ ከተገኘ ኩባንያው 70 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያገኝ ሎክ ተናግረዋል።
"የእኛ ኃላፊነት እና ቁርጠኝነት ለተጎጂ ቤተሰቦች ነው" ብለዋል ሎክ።"ይህ ጊዜ ስብርባሪ የሚገኝበት እና ለቤተሰቦቻቸው የምናሳውቅበት ይሆናል የሚል ተስፋ አለን።"
የማሌዥያ ባለስጣናት መጀመሪያ ላይ አውሮፕላኑ ጠለፋ ሳይፈጸምበት እንደማይቀር ሲናገሩ ነበር።
የተወሰኑ ያልተረጋገጡ እና የተወሰኑ ደግሞ የአውሮፕላኑ ናቸው ተብለው የሚታመኑ ስብርባሪዎች በአፍሪካ የባህር ዳርቻዎች እና በህንድ ውቅያኖስ በሚገኙ ደሴቶች ተንሳፈው ተገኝተዋል።
ከ150 በላይ ታሳፋሪዎቹ ቻይናውያን የነበሩ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው የማሌዥያ አየርመንገድ፣ ቦይንግ፣ የአውሮፕላን ሞተር ሰሪ ሮልስ ሮይስ፣ አሊያንዝ ኢንሹራንስ ቡድን ሌሎችም ካሳ እንዲከፍሏቸው ጠይቀዋል።
በ 2018 ማሌዥያ ኦሽን ኢንፊኒቲ አውሮፕላኑን የሚያገኝ ከሆነ 70 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ተስማምታ ነበር፤ ነገርግን ሁለት ጊዜ ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም።
ከእዚያ ቀጥሎ ማሌዥያ፣ ቻይና እና አውስትራሊያ በደቡብ ህንድ ወቅያኖስ ኢንማርሳት ሳተላይት እና አውሮፕላን በማገናኘት በ120 ስኩየር ኪሎሜትር የሸፈነ ፍለጋ አድርገው ነበር።