በአሮጌ መዝገብ ቤት የተገኘው የአሜሪካ ህገመንግስት ቅጅ በ9 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ
ቅጅው በካሊፎርንያ በሚገኘ ታሪካ ህንጻ ውስጥ ባለ አሮጌ መዝገብ ቤት መደርደሪያ ላይ ነበር በ2022 የተገኘው
የህገመንግስት ቅጅው 237 አመት እድሜ ያለው ነው ተብሏል
በአሮጌ መዝገብ ቤት የተገኘው አሜሪካ ህገመንግስት ቅጅ በጨረታ ተሸጠ።
237 አመታት እድሜ ያለው የአሜሪካ ህገ መንግስት ቅጅ በጨረታ በዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር መሸጡን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቅጅው በካሊፎርንያ በሚገኘ ታሪካ ህንጻ ውስጥ ባለ አሮጌ መዝገብ ቤት መደርደሪያ ላይ ነበር በ2022 የተገኘው።
በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ ግዛቶች ስብበሳ ካደረጉ በኋላ የአሜሪካ ፌደራል መንግስት መመስረቻ ይሆናል ያሉትን ይህን ህገመንግስት በ1787 አዘጋጅተዋል። እንዲህ አይነት ስምንት ቅጅዎች አሉ ተብሎ የሚታመን ሲሆን ሰባቱ በህዝብ እጅ እንዳሉ ተገልጿል።
ጨረታውን በስልኩ የተሳተፈው ገዥ ማንነቱ አልታወቀም።
ቅጅው የተገኘው ህገመንግስቱ በሚጻፍበት ወቅት ንብረትነቱ የሳሙኤል ጆንሰን በሆነ ታሪካዊ የልማት እርሻ ቦታ ላይ ነው።
1983 በዚሁ ቦታ ላይ የተገኘው የነጻነት አዋጅ ቅጅ በ412 ዶላር የተሸጠ ሲሆን የህገመንግስቱ ቅጅ ግን እስከ 2022 ሳይገኝ ቀርቷል።
ከህገመንግስቱ ቅጅ ጋር በአሜሪካው መስራች ፕሬዝደንት ጆርድ ዋሽንግተን የተፈረመ ሁሉም ግዛቶች ሰነዱን እንዲያጸደቁት የሚጠይቅ ደብዳቤ ተገኝቷል።
"ሁለም የነጻነት መብቶችን እንዲያገኝ፣ ግለሰቦች የተወሰነ የነጻነት ድርሻቸውን መተው አለባቸው" ሲሉ ጽፈዋል ዋሽንግተን።
እንዲህ አይነት የአሜሪካ ህገመንግስት የተገኘው በ1891 ሲሆን በ400 ዶላር ነበር የተሸጠው።
ጨረታው የተካሄደው በአሽቪሌ ሲሆን ባለፈው ወር በግዛቷ የተነሳው አውሎንፋስ ከፍተኛ ወድመት በማስከተሉ ምክንያት ዘግይቶ ነበር።