በቻይና ልጁን ሒሳብ ትምህርት በማስጠናት ላይ የነበረ ወላጅ ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገብቷል
በቻይና ልጆቻቸውን የሚያስጠኑ ወላጆች ለልብ ህመም እየተዳረጉ ነው ተብሏል፡፡
ልጆቻቸው ጎበዝ እና አስተዋይ እንዲሆኑ የወላጆች ምኞት ሲሆን ለዚህ እንዲበቁ ደግሞ የዕለት ክትትሎችን ያደርጋሉ፡፡
ከነዚህ መካከል አንዱ ደግሞ የቤት ስራዎችን መከታተል፣ ያልገባቸውን ማስረዳት እና የፈተናዎች አካባቢ ማስጠናት ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በቻይና ልጆቻቸውን በማስጠናት ላይ እያሉ እንደ ልብ እና መሰል ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው ለህክምና ክትትል ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ወላጆች እንዳሉ ተገልጿል፡፡
ከሰሞኑ ዛንግ የተሰኘ የ40 ዓመት ቻይናዊ ወላጅ ልጁን ለፈተና እያዘጋጀ እያለ ህመም አጋጥሞት ሆስፒታል እንደገባ የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ከ1 ሚሊየን በአንዷ የሚፈጠር አስገራሚ ክስተት - በሁለት ማህጸን መጸነስ
እንደ ዘገባው ከሆነ ይህ ወላጅ የሂሳብ ትምህርትን ለልጁ በማስጠናት ላይ እያለ ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገብቷል ተብሏል፡፡
በሐኪሞች እርዳታ ህይወቱ ለጥቂት ተርፏል የተባለው ይህ ወላጅ በጭንቀት ምክንያት የልብ ህመም እንዳጋጠመው ተናግረዋል፡፡
ሌሎች ልጆቻቸውን በማስጠናት ላይ የነበሩ ወላጆችም እንደ ስትሮክ እና መሰል ከባድ ህመሞች እየተዳረጉ ነው የተባለ ሲሆን ቻይና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎቿ የምትሰጠው ትምህርት ከባድ መሆን ወላጆችን እያስጨነቀ ነውም ተብሏል፡፡