እነዚህ ሚስጢራዊ ኮዶች በግልጽ ያልተቀመጡ እና የተደበቁ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላሉ
በአለም አቀፍ ደረጃ ከ3 ቢሊየን በላይ ስማርት ስልኮች አገግሎት እየሰጡ ነው።
ከ70 በመቶ በላይ የስማርት ስልክ ገበያውን የተቆጣጠሩት አንድሮይድ ስልኮች፥ በርካታ ዩ ኤስ ኤስ ዲ
ወይም ሚስጢራዊ ኮዶች እንዳሏቸው ይነገራል።
ሚስጢራዊ ኮዶቹ በአንድሮይድ ስማርት ስልኮች ውስጥ የተደበቁ አገልግሎቶችን ለማግኘት ያስችላሉ።
በስልኮቹ ላይ የተቀመጡ መረጃዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ ኮዶችም አሉ።
እነዚህን ሚስጢራዊ ኮዶች በአግባቡ ጽፎ በመደውል የሚፈለገውን ግልጋሎት ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጹ ባለሙያዎች ፥ አንዳንዶቹ ኮዶች ሁለት ጊዜ ማሰብን ሊጠይቁ እንደሚችሉ ያሳስባሉ።
በተለይም የስልክን ሙሉ በሙሉ የሚያጠፉ ኮዶችን አስፈላጊ ካልሆነ መጠቀም አይገባም ነው የሚሉት።
በቀጣይ የተዘረዘሩት ሚስጢራዊ ኮዶችም አንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚገኙ በቀላሉ የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነትን ለማረጋገጥ እና የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት የሚያስችሉ ናቸው።
1. *#06# - የስልክን አለም አቀፍ መለያ (አይ ኤም ኢ አይ) ቁጥር ለማወቅ
2. *#61# ፣ *#62# ወይም #004# - የስልክ ጥሪ ወደሌላ ሰው ስልክ መተላለፉን (call forwarding) ለማረጋገጥ
3. ##61# ወይም ##67# - ያላነሳናቸው የስልክ ጥሪዎች በሌሎች ተነስቷል ብለን ስናምን፣ ስልካችን ሲዘጋ ጥሪው ወደ ሌላ ስልክ ሲያመራ( call forwarding) ወይም ስልካችን መጠለፉን ስንጠረጥር ለማጥፋት
4. *#21# - የስልክ ጥሪያችን በሌሎች አለመጠለፉን ለማረጋገጥ
5. ##21# - ስልካችን ተጠልፏል ብለን ስናምን ለማቋረጥ
6. #0# - የስማርት ስልኮች ስክሪን፣ ካሜራ፣ ንዝረት፣ ሴንሰርን ጨምሮ ሌሎች ነገሮች ለመሞከር
7. *31# - የደዋዩን ማንነት ለመደበቅ (Disable Caller ID)
8. #31# - የደዋዩን ማንነት መደበቅ ለማቋረጥ
9. *43# - ተጨማሪ የስልክ ጥሪን ለማስተናገድ (Enable Call Waiting)
10. #43# - ተጨማሪ የስልክ ጥሪን ለማስተናገድ የሚያስችለውን እድል ለማቋረጥ (Disable Call Waiting)
11. *#1234# - የስልክ ሞዴልና የተመረተበትን አመት ለማወቅ
12. *#0228# - የስማርት ስልኮችን ባትሪ መረጃ ለማየት
13. ##7780## - የስልክ መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት (በተለይ የግል መረጃዎች እና መተግበሪያዎች በማጥፋት ስልኩን ለመሸጥ)