አንጎላ ከነዳጅ ላኪ ሀገራት ማህበር በመውጣት ሶስተኛዋ ሀገር ልትሆን ነው
የአንጎላ መውጣት የኦፔክ የአባል ሀገራትን ቁጥር ወደ 12 ዝቅ ሲያደርግ በአጠቃላይ የምርት መጠኑን ደግሞ ወደ በቀን 27 ሚሊዮን በርሜል እንዲቀንስ ያደርገዋል
አንጎላ በ2020 ከወጣችው ኢኳዶር እና 2019 ከወጣች ኳታር በመቀጠል ከአባልነት በመውጣት ሶስተኛ ሀገር ትሆናለች
አንጎላ ከነዳጅ ላኪ ሀገራት ማህበር በመውጣት ሶስተኛዋ ሀገር ልትሆን ነው።
አፍሪካዊቷ አንጎላ ከነዳጅ ላኪ ሀገራት ማህበር (ኦፔክ) እንደምትወጣ አስታወቀች።
አንጎላ በ2020 ከወጣችው ኢኳዶር እና 2019 ከወጣች ኳታር በመቀጠል ከአባልነት በመውጣት ሶስተኛ ሀገር ትሆናለች።
በ2007 ኦፔክን የተቀላቀለችው አንጎላ በቀን 1.1 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ በቀን ታመርታለች።
ኦፔክ በሳኡዲ አረቢያ፣በኩየት፣ በቬንዙዌላ፣ በኢራቅ እና በኢራን በ1960 የተመሰረተ ሲሆን በ2017 ከሩሲያ እና ከሌሎች አባል ካልሆኑ ሀገራት ጋር ኦፔክ ፕላስ በሚል ማዕቀፍ ገበያውን ለመቆጣጠር በማሰብ መስራት ጀምራል።
የአንጎላ መውጣት የኦፔክ የአባል ሀገራትን ቁጥር ወደ 12 ዝቅ ሲያደርግ በአጠቃላይ የምርት መጠኑን ደግሞ ወደ በቀን 27 ሚሊዮን በርሜል እንዲቀንስ ያደርገዋል።
አንጎላ በቅርብ አመታት ውስጥ ኢንቨስትመንት በመቀነሷ ምክንያት በኦፔክ ፕላስ የተቀመጠውን የምርት ኮታ ማሟላት አልቻለችም ነበር።
አንጎላ ትንሽ ምርት ያላቸውን ሌሎች ሀገራት ልትቀላቀል ትችላለች ተብሏል።
ትንሽ ምርት ያላቸው ሀገራትም ኦፔክ ፕላስን ሲቀላቀሉ ይታያል። ኢኳቶሪያል ጊኒ በ2017 መሉ አባል ስትሆን ጋቦን ደግሞ በ2016 በድጋሚ ገብታለች። ካን ከ2018-22 ፖኪስታንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት መርተዋል።