ግሮሲ እንዳሉት በቀጥታ በቦታው መግባት በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ኑክሌር ማብላያው ስራ መጀመሩን ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል
ስለ2ኛው የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ማብላያ ጣቢያ ምን ተባለ?
አለምአቀፉ የኑክሌር ተቆጣጣሪ ድርጅት (አይኤኢኤ) ሁለተኛው የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ማብላያ ጣቢያ ስራ የጀመረ ይመስላል ብሏል።
ድርጅቱ በሰሜን ኮሪያ ዮንግቢዮን በሚገኘው ኑክሌር ኮምፕሌክስ ያለው ማብላያ ለመጀመሪያ ጊዜ አቶሚክ ፊውል ተጠቅሟል፤ ይህም ሀገሪቱ ለኑክሌር መሳሪያዎች ፕሉቶኒየም የመጠቀም አቅም እንዳላት ያሳያል ብሏል።
ሰሜን ኮሪያ ለአመታት የኑክሌር የጦር መሳሪያ ለመስራት ፕሉቶኒየም ስትጠቀም እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።
ከጣቢያው "የሚለቀቀው የሞቀ ውሃ የሚያሳየው ማብላያው ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ ነው" ሲሉ የድርጅቱ ኃላፊ ራፌኤል ግሮሲ ባወጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ፒዮንያንግ የኑክሌር ተቆጣጣሪ ሰራተኞችን ካባረረችበት ከፈረንጆቹ 2009 ጀምሮ ድርጅቱ በሰሜን ኮሪያ መግባት አልቻለም።
ድርጅቱ አሁን ላይ ከሩቅ ሆኖ በሳተላይት አማካኝነት ነው እየተከታተለ ያለው።
ግሮሲ እንዳሉት በቀጥታ በቦታው መግባት በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ኑክሌር ማብላያው ስራ መጀመሩን ማረጋገጥ አይቻልም ብለዋል።
ድርጅቱ ከባለፈው ጥቅምት ጀምሮ ከማብላያው የማቀዝቀዧ ሲስተም ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ ሲለቅ መመልከቱን እና ይህም ማብላያው ስላ መጀመሩን የሚያመለክት ነው ሲል ገልጿል።
ግሮሲ እንደተናገሩት የሚለቀቀው ውሃ ሙቅ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎችን እንዳሉም ተናግረዋል።
ሰሜን ኮሪያ ስድስት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ አድርጋለች ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ እና የአሜሪካ ጥምረት እንደሚያሰጋት የምትገልጸው ሰሜን ኮሪያ፣ ራሷን ለመከላከል ኑክሌር እንደምጠቀም ስትገልጽ ቆይታለች።