የቀድሞው የአንጎላ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር በሙስና ክስ 14 አመታት እስር ተፈረደባቸው
የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትርም ቀደም ሲል 14 አመታት እስር ተፈርዶባቸዋል
የቀድሞው የአንጎላ የኮሙኒኬሽን ሚኒስትር በሙስና ክስ ምክንያት ለ14 አመታት እስር ተዳርገዋል
አንጎላ ያሰረቻቸው ሚኒስትር የቀድሞ የሀገሪቱ የኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትሩ ማኑኤል ራበልያስ ሲሆኑ የታሳሩበት ምክንያትም በሙስና ተዘፍቀዋል በሚል ነው፡፡
ጥፋተኛ የተባሉት ሚኒስትር የ14 ዓመታት እስራት እንደተበ የነባቸውም ነው የአፍሪካን ኒውስ ዘገባ የሚያመለክተው፡፡ እ.ኤ.አ 2017 ፕሬዝዳንት ጆአው ሎረንኖ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ሁለተኛው የታሰሩ የቀድሞ ሚኒስትር ያደርጋቸዋልም ተብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ጆአው ሎረንኖ አንጎላን ለ38 ዓመታት የመሯት ጆዜ ኤድዋርዶ ዶሳንቶስን በመተካት ከአምስት አመታት በፊት መንበረ ስልጣኑን መቆጣጠራቸው የሚታወቅ ነው፡፡
ከስልጣናቸው ማግስት ከፍተኛ የሆነ የፀረ ሙስና ዘመቻ መጀመራቸው፤ በዚህም የቀድሞ ፕሬዝዳንት ልጅ ጨምሮ ለስርአቱ ቅርብ የተባሉ እና ቁልፍ ቦታዎች ላይ የነበሩ ሰዎች እንዲጠየቁ እስከማድረግ ደርሰዋል፡፡
ማኑኤል ራበልያስ ከእነዚህ ባለስልጠናት አንዱ የነበሩ ሲሆን፤ በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርና የህዝብን ሀብት በማባከን በሚል ምክንያት በሉዋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፈረንጆቹ ጥቅምት 2020 በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡
ከ2016 እስከ 2017 በነበሩ ጊዝያት ብቻ የ98 ሚልዮን ዩሮ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ክስ ቀርቦላቸው የ14 ዓመታት እስር እንደተበየነባቸውም ነው የተገለፀው፡፡
እንደ ማኑኤል ራበልያስ ሁሉ የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር አውግሰቶ ዳ ሲልቫ እ.ኤ.አ በ2019 የ14 ዓማታት እስር እንደተፈረደባቸው የሚታወስ ነው፡፡