ንጉሱ በስኳር ህመም ምክንያት ለሳምንታት በሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ህይወታቸው አልፏል
የ72 ዓመቱ ንጉስ ጉድዊል ዘዌልቲኒ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን የንጉሳውያን ቤተ መንግስት ዛሬ ጠዋት አረግጧል።
ንጉስ ጉድዊል ዘዌልቲኒ በስኳር ህመም ምክንያት ለሳምንታት በሆስፒታል ህክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን እና በዛሬው እለት ጠዋት ላይ ህይወታቸው ማለፉንምን እንደተነገረም ሲቲጂኤን ዘግቧል፡፡
የንጉሳውያኑ ቤተሰቦች ንጉሱ በታመሙበት ወቅት በጸሎት ከጎናቸው ለነበሩ ደቡብ አፍሪካውያን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳም በዙሉ ንጉስ ጉድዊል ዘዌልቲኒ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን መግለጻቸው ተነግሯል።
ንጉስ ጉድዊል ዘዌልቲኒ በዙሉ ንጉሳውያን ዘንድ ረጅም ዓመት በንግስና ማገልገላቸው የሚነገር ሲሆን- ከ5 አስርት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ በስልጣን ቆይተዋል።
በአውሮፓውያኑ በ1948 የተወለዱት ንጉስ ጉድዊል ዘዌልቲኒ በፈረንጆች 1968 የአባታቸውን ህልፈት ተከትሎ ነው በ20 ዓመታቸው የንግስናው ዙፋን ላይ የተቀመጡት።ሆኖም ግን የንግስናውን አክሊል የደፉት ከ3 ዓመታት በሁዋላ በ1971 ሲሆን፤ምክንያም ደግሞ የግድያ ሙከራ ጥርጣሬ በመኖሩ ለ3 ዓመታት ከቤተ መንግስት ውጪ ተደብቀው በመቆየታቸው ነው።