ስፖርት
ካፍ የቻድ መንግስት በእግር ኳስ ጣልቃ ገብቷል በሚል ሀገሪቱን ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ አደረገ
የቻድ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኃላፊነት እንዲነሱ አድርገዋል
የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ቻድን ከዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ሊያግዳት ይችላል
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ቻድን ከ2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውጭ ማድረጉ ተሰምቷል።
ካፍ ውሳኔውን ያሳለፈው የቻድ መንግስት በሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳይ ጣልቃ ገብቷል በሚል እንደሆነ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።
ከየቻድ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር ስልጣናቸውን በመጠቀም ባሳለፍነው መጋቢት 13 ቀን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኃላፊነት ማንሳታቸው ተነግሯል።
ይህንን እርምጃ ተከትሎም የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ቻድን ከዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ ሊያግዳት ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።
የቻድ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ቻድ ከማሊ፣ ጊኒ እና ናቢያ ጋር በምድብ 1 የተደለደለች ሲሆን፣ እስካሁን ባደረገችው ጨዋታ 1 ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻለችው።
ከምድቧ ባላት አነስተኛ ነጥብ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪ መውጣቷን ከወዲሁ ያረጋገጠች ቢሆንም፤ በቀጣይ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከናሚቢያ እና ከማሊ ጋር በሚኖራት ጨዋታም ለሀገራቱ ፎረፌ እንዲሰጥም ካፍ ወስኗል።