በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አነስተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ታድሟል
በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አነስተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ታድሟል
በየአመቱ መስከረም ወር የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በዛሬው እለት ተከብሯል፡፡ ለወትሮው በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚሳተፍበት የኢሬቻ በዓል ዘንድሮ ቁጥሩ አነስተኛ የሆነ ህዝብ ነው የተገኘው፡፡
ዘንድሮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ በመከሰቱ ምክንት የበዓሉ ተሳታፊዎች ቁጥር አነስተኛ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባስተላለፈው መልእክት በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ኮሮና እንዳይስፋፋ ማድረግ ይገባል ማለቱ ይታወሳል፡፡ መንግስትም የተሳተፊዎች ቁጥር ይህንኑ መነሻ በማድረግ አነስተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንዲሳተፍ አድርጓል፡፡
በበዓሉ ላይ ለመታደም የበዓሉ አክባሪዎች ወደሚከበርበት በማለዳ ቦታ አምርተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ አባገዳዎች፤ወጣቶች፣ ሴቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ በዓሉ በነገው እለት በቢሾፍቱ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡