በፈረንጆቹ 2006 ሼክ ሰባህ አሚር ሆነው ሲሾሙ ሼክ ንዋፍ አል አህመድ አልሳበህ ደግሞ በአልጋ ወራሽነት ተመረጡ
በፈረንጆቹ 2006 ሼክ ሰባህ አሚር ሆነው ሲሾሙ ሸክ ንዋፍ አል አህመድ አልሳበህ ደግሞ በአልጋ ወራሽነት ተመረጡ
የኩዌቱ አልጋ ወራሽ ሼክ ንዋፍ አል አህመድ አልሳባህን በዛሬው እለት በሞቱት አሚር ሼህ ሰባህ አል አህመድ አል ጃቢር አል ሳባህ ቦታ ምትክ ሆነው መሾማቸውን የኩየት ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
ሼክ ንዋፍ አል አህመድ አልሳበህ በፈረንጀቹ 2006 አልጋ ወራሽ ሆነው ሲሾሙ ሼክ ሳባህ ደግሞ ኢሚር ሆነው ተሾመው ነበር፡፡
በኩዌት ህግ መሰረት እያንዳንዱ አዲስ ልኡል አልጋ ወራሽ በሀገሪቱ ብሄራዊ ምክር ቤት በአብላጫ ድምጽ መጽደቅ አለበት፡፡ በኩዌት አልጋ ወራሽና ኢሚር የሙባረክ አል ሳባህ ነገድ አባል እና ዘመድ ለሆኑ ብቻ የተተወ ነው፡፡
ዛሬ ህይወታቸው ያለፈው አሚር ከሰሞኑ በጠና ታመው ህክምና ላይ እንደነበሩ ተዘግቧል፡፡ በሃገሪቱ የሚገኙ የብዙሃን መገናኛ ጣቢያዎች የዕለቱን መደበኛ ስርጭታቸውን በማቋረጥ መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው ዝግጅቶችን ሲያሰራጩ ነው የዋሉት፡፡
እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ ሃገራቸውን በአሚርነት የመሩት ሼህ ሰባህ በ91 ዓመታቸው ማረፋቸውን የህይወት ታሪክ መረጃዎቻቸው አመልክተዋል፡፡