ውድድሩ እስከመጨረሻው ዙር ይደርሳል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም ሁለተኛው ዙር ላይ ተጠናቋል
ተጠባቂው የቦክስ ውድድር በአንቶኒ ጆሽዋ አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
በትናንትናው ዕለት በነዳጅ ሀብታሟ ሀገር ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ከባድ የቦክስ ፍልሚያ እንደሚካሄድ ተገልጾ ነበር፡፡
ይህ ውድድር በትውልደ ናይጀሪያዊው እና በዜግነት ብሪታንያ የሆነው አንቶኒ ጆሽዋ ከካሜሩኑ ፍራንሲስ ንጋኑ መካከል ተካሂዷል፡፡
ዓለም በጉጉት ሲጠብቀው የነበረው ይህ የከባድ ሚዛን ቦክስ ውድድር የ34 ዓመቱ አንቶኒ ጆሽዋ በዝረራ ማሸነፍ ችሏል፡፡
70 ሚሊዮን ዶላር ለቅድመ ውድድር ወጪ የተደረገበት ይህ ውድድር ሁለቱም ተፋላሚዎች ከዚህ በፊት ስኬታማ መሆናቸውን ተከትሎ ውድድሩ ከዝረራ ይልቅ እስከ መጨረሻው ይቀጥላል ተብሎም ተጠብቆ ነበር፡፡
የሁለቱ ቢሊየነሮች የቦክስ ፍልሚያ በኤክስ በቀጥታ እንደሚተላለፍ መስክ ገለጸ
ይሁንና አንቶኒ ጆሽዋ በንጋኑ ላይ ባደረሰው ከባድ ምት በመንገዳገድ የተጀመረው ይህ ውድድር ሁለተኛው ዙር ላይ ራሱን ስቶ ለመውደቅ ተገዷል፡፡
ጆሽዋ ማሸነፉን ተከትሎ ታይሰን ፉሪን በቀጣይ እንደሚገጥም የሚጠበቅ ሲሆን የፊታችን ግንቦት ወር ላይ እንደሚፋለሙ ይጠበቃል፡፡
አሸናፊው ጆሽዋ ከውድድሩ በኋላ በሰጠው አስተያየት ንጋኑ ከባድ ቦክሰኛ መሆኑን አውቃለሁ፣ ከታይሰን ፉሪ ጋር እስከ መጨረሻው ድረስ ያደረገውን ፍልሚያ አስታውሳለሁ ብሏል፡፡
ንጋኑ በመሸነፉ ምክንያት ውድድር እንዳያቆም ነግሬዋለሁ ያለው ጆሽዋ አሰልጣኜ በሚለኝ መሰረት በቀጣይ ውድድሮች ለይ እሳተፋለሁ ሲል ተናግሯል፡፡