አሜሪካ በርካታ ዜጎቿን በማዋከብ፣ በማሰር እና በማፈናቀል ዚምባብዌን ከሳለች
አሜሪካ ዚምባቡዌ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቼን አባረረች ስትል ከሰሰች።
አሜሪካ በእርዳታ ስራ ላይ ተሰማርተው ዜምባቡዌ ውስጥ የነበሩትን በርካታ ዜጎቿ ላይ የማዋከብ፣ የማሰር እና የማፈናቀል ተግባር ተፈጽሞባቸዋል ብላለች።
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) የዚምባቡዌ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቀጣሪዎቻቸው በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የአሜሪካ ዜጎች ላይ "በቃል እና በአካል" ማስፈራሪያ እና ዛቻ አድርሰውባቸዋል ብሏል።
የአሜሪካ ዜጎች በዚምባቡዌ የሚገኙት የሲቪክ ተቋማትን ተሳትፎ ለማገዝ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብት ተቋማትን ለመገደፍ ነው እዛ እንደሚገኙ ዩኤስኤአይዲ አስታውቋል።
ነገር ግን የዚምባብዌ በሀገሪቱ ያለውን የዲሞክራሲያ ባህል ማሻሻያ ለማድረግ የነበራት ቁርጠኝነት ባዶ ነበር ብሏል።
የዚምባቡዌ መንግስት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ክስ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
አሜሪካ ባሳለፍነው ሰኞ የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ኢመርሰን ምናንጋግዋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ላይ በመብት ጥሰት ተሳትፈዋል በሚል ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።
ፕሬዝደንቱ እና ባለስልጣናቱ በአሜሪካ ሀገር ያለ ንብረት እንዳያንቀሳቅሱ እና ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የሚያደርገው ይህ ማዕቀብ ለሁለት አስርት አመታት ተጥሎ የነበረውን ማዕቀብ የሚተካ መሆኑንም ተነግሯል።
በዚምባቡዌ እየተፈጸመ ያለው ሙስና እና የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሚያሳስባቸው የገለጹት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አዲሱ እርምጃ እየተወሰደ ያለው ጠንካራ የፖሊሲ ማዕቀብ አካል ነው ብለዋል።
"የዚምባቡዌ መንግስት አባላትን ጨምሮ ቁልፍ ባለስልጣናት ለተፈጸመው የመንግስት ሀብት ዝርፊያ ኃላፊነት ይወስዳሉ" ሲሉ ብሊንከን ተናግረዋል።
የዚምባቡዌ ፕሬዝደንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ የአሜሪካ ማዕቀብ የጠላት ውሳኔ በማለት ያወዘጉ ሲሆን፤ የአሜሪካን መንግስም ያለ በቂ ማስረጃ ስም እያጠፋ ነው ሲሉ ከሰዋል።