የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉተረ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በይፋዊ ጉብኝታቸው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም ይጠበቃል።
በተጨማሪም ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩም ይጠበቃል።
አንቶኒ ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጰያ የነበረውን ጦርነት ለማስቆም በተደረገው ስምምነት አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎም ይጠበቃል።