የዩጋንዳዊቷ ፎቶ መቆረጥ መነጋገሪያ ሆነ፡፡
ዩጋንዳዊቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ቫኔሳ ናካቴ በዳቮስ በእንግድነት በተገኘችበት የአየር ንብረት ላይ ያተኮረ ዝግጅት ከሌሎች ነጭ አጋሮቿ ጋር የተነሳችው ፎቶ ተቆርጦ መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
የዜና ዘገባ በመስራት ላይ የነበረው አሶሺየትድ ፕረስ በፎቶው ዳርላይ የነበረችውን ቫኔሳን ቆርጦ በማውጣት የነጮቹን ብቻ በመጠቀሙ ይቅርታ ጠይቋል፡፡
ግለሰቧ በትዊተር ገጿ ዘረኝነት የሚለውን ቃል ትርጉም ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት አሁን ነው የተቆረጠው የኔ ምስል ብቻ ሳይሆን አህጉሬና የአህጉሬ ሀሳብም ነው ብላለች፡፡
ቬኔሳ የዜና ምንጩን ለምን ይህን እንዳደረገም ጠይቃለች፡፡ ይህ የፎቶ መቆረጥ ብቻ ሳይሆን የሀሳብም መቆረጥ ነው፣ ነገር ግን እኔ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል ስትልም ተናግራለች፡፡
በአሶሼትድ ፕረስ ከፍተኛ ኤዲተር ሳሊ ቡዝቤ ከሙሉ ፎቶው የቀለም ልዩነት የፈጠረችው የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ፎቶ በመቆረጡ ይቅርታ ጠይቀው ለዘጋቢዎች ምን መካተትና መወገድ እንዳለበት ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ እንዲህ አይነት አጋጣሚዎች ፈፅሞ ተቀባይነት እንደሌላቸውና የተቋሙ ሰራተኞች ትምህርት ያገኙበት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፡- ሲኤንኤን