ታብሌቱ ለማስተማሪያ የሚውል እና የመጽሐፍ ወጪን የሚያስቀር ነው
ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን የተነደፈው ታብሌት ለእይታ በቃ
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ ያሠራው የማሳያ ታብሌት (prototype) የሙከራ ምርቱ ለእይታ በቅቷል።
ታብሌቱ ከ9ኛ እስከ 12 ክፍል ላሉ ተማሪዎች እና መምህራን መማሪያ እና ማስተማሪያነት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን የተነደፈው ታብሌት መንግሥት ለመጽሐፍ የሚያወጣውን ወጪ ለማስቀረት እንደሚያግዝ ሚኒስቴርሩ አስታውቋል።
ተማሪዎች ራሳቸውን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲያስተዋውቁ ለማድረግ ያስችላልም።
ታብሌቱን ወደ ተግባር ለማስገባት ግን የኢንተርኔት ግንኙነት ጉዳይ በእጅጉ አሳሳቢ ነው ፡፡ ሆኖም ሚኒስቴሩ ችግሩን ለመፍታት እሠራለሁ ብሏል።
እስከ 70 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴትን ይጠቀማል የተባለውን ታብሌቱን ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ለማምረት እቅድ ስለመያዙም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።