23ኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው ጎግል ከዛሬ ጀምሮ ‘አሮጌ’ አንድሮይዶችን በሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ላይ አይሰራም
ውሳኔው የተጠቃሚዎቹን ደህንነት ለመጠበቅ እያደረገ ያለው ቀጣይ ጥረት አካል እንደሆነም ገልጿል
አንድሮይድ 2.3 እና ከዚያ በታች የሚጠቀሙ ስልኮች ከዛሬ ጀምሮ የጎግል ማፕ፣ ዩ ቲዩብ እና የጂ ሜይል አግልግሎቶቹን እንደማያገኙም ኩባንያው አስታውቋል
ጎግል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስማርት ስልኮች ላይ አገልግሎቶቹን ሊያቆም መሆኑ ተሰማ፡፡
ኩባንያው ከዛሬ ጀምሮ የጎግል ማፕ፣ ዩ ቲዩብ እና የጂ ሜይል አግልግሎቶቹን በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ስማርት ስልኮች ላይ ያቆማል ነው ያለው የእንግሊዙ ዘ ሰን ጋዜጣ።
በዚህም ከሰዓታት በሁዋላ በርካታ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች እነዚህን አግልግሎት ከመጠቀም ይታገዳሉ ተብሏል።
አግልግሎቱን እንዳያገኙ የሚታገዱት ስማርት ስልኮችም ከዓመታት በፊት የተለቀቀውን አንድሮይድ 2.3 እና ሌሎችንም ከእሱ በፊት ስራ ላይ የዋሉ መተግበሪያ ስርዓቶችን (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) የሚጠቀሙ ስልኮች ናቸው ተብሏል።
ጎግል ኢትዮጵያዊቷን የኮምፒዩተር ሳይንቲስት ከስራ ማሰናበቱ እያነጋገረ ነው
ስልኮቹ ከዛሬ መስከረም 27 በኋላ (በፈረንጆቹ) ወደ ጎግል ማፕ፣ ዩ ቲዩብ እና ጂ ሜይል ለመግባት ቢሞክሩ እንደማይችሉ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
የስልኮቹን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማሻሻል ካልተቻለ እነዚህን አገልግሎቶች በስማርት ስልኮቹ ላይ ማግኘት እንደማይቻልም ነው ጎግል ያስታወቀው።
ሁዋዌ ‘ሀርመኒ’ የተባለ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስራ ላይ አዋለ
“Username or password errors” የሚል ምላሽ ይጠብቃችኋልም ብሏል፡፡
ከውሳኔው ላይ የተደረሰውም የደንበኞቼን ደህንነት ለመጠበቅ ነው ያለው ጎግል፣ እድሜያቸው የገፉ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ለመረጃ ጠላፊዎች ተጋላጭ ናቸው ብሏል።
ጎግል አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 23ኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል፡፡