የአፕል አክሲዮን በዚህ ዓመት በ49 በመቶ ጨምሯል
የአፕል ኩባያ ዋጋ 3 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ግብይት አደረገ። ኩባንያው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰ ብቸኛው ድርጅት ሆኗል።
የአፕል አክሲዮኖች በ193.97 ዶላር ክብረ-ወሰን በመያዝ ከሁለት በመቶ በላይ ጨምሯል። በ15.7 ቢሊዮን አክሲዮኖች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ኩባንያው ወደ ታሪካዊ የገበያ እሴቱ ገብቷል።
አፕል ከዚህ በፊት እዚህ ስኬት ላይ አንድ ጊዜ ብቻ መድረሱ ተነግሯል።
ባለፈው ዓመት አፕል በአንድ ቀን ግብይት ወቅት የሦስት ትሪሊዮን ዶላር ቢደርስም፤ መቆየት ግን አልቻለም።
ከሰሞኑን የኩባንያው አክሲዮን ለሦስተኛ ተከታታይ ቀናት በከፍተኛ መሸጡን ሲኤንኤን ዘግቧል።
አፕል በአርብ ገበያ ሦስት ትሪሊዮን ዶላር ለመድረስ ከሚያስፈልገው 190.73 ዶላር በቀላሉ አልፏል ተብሏል።
ለግዙፉ ቴክኖሎጂ የከፍተኛ ዋጋ ያስመዘገበው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ "አፕል ቪዥን ፕሮ" የተሰኘ ስጋት ያሳደረ ምርቱን ባስተዋወቀ ማግስት ነው።
የአፕል አክሲዮን በዚህ ዓመት በ 49 በመቶ ጨምሯል። ይህም ባለሀብቶች ወደ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አይናቸውን በመጣላቸወሸ ነው ተብሏል።
የዚህ ዓመት የአፕል አክሲዮን ገበያ ስኬት ከ2022 ጋር የተቃረነ መሆኑን ተጠቁሟል። በ2023 መጀመሪያ ላይ የአፕል የገበያ ዋጋ ከ2021 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለት ትሪሊዮን ዶላር በታች ወርዷል።