የውድድሩ ጊዜ የተዛወረው በኮሮና ቫይረስ ስጋት ነው
ቦስተን ማራቶን ወደ መስከረም ተዛወረ
በየዓመቱ ወርሃ ሚያዘያ በገባ በሁለተኛው ሳምንት የመጀመሪያ ቀን እለተ ሰኞ የሚካሄደው የቦስተን ማራቶን ወደ ወርሃ መስከረም ተዘዋውሯል፡፡
እ.ኤ.አ ከ1897 ጀምሮ የአርበኞችን ቀን ታሳቢ አድርጎ ሲካሄድ የነበረውን ውድድር ዘንድሮ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በተለመደው ወቅት ማካሄድ አልተቻለም ተብሏል፡፡
ውድድሩ ከወትሮው በተለየ መልኩ ከወርሃ ሚያዚያ ውጭ ሲካሄድ በባለፉት አንድ መቶ አመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም የአሜሪካ ብሄራዊ ሬዲዮ ዘግቧል፡፡
በ1918 ብቻ በአንደኛው የዓለም ጦርነት የተሳተፉ ወታደሮችን ለማስታወስ ሲባል በተዘጋጀ የዱላ ቅብብል ውድድር ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ ተዛውሯል፡፡
ከ1997 እስከ 1999 የተካሄዱ የማራቶኑን ውድድሮች በተከታታይ ያሸነፈችውን የ‘ቦስተኗ ንግስት’ ፋጡማ ሮባን ጨምሮ ሌሊሳ ዴሲሳ እና ለሚ ብርሃኑን መሰል ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን ማሸነፋቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡