አረብ ኢምሬትስ የሰማዕታት ቀን አከበረች
አረብ ኢምሬትስ በውስጥም በውጭም ሀገራዊ ግዴታቸውን ሲወጡ ህይወታቸውን የከፈሉትን ዜጎቿን መስዋዕትነት አክብራለች
ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዘይድ በሰማዕት ቀን ጀግኖች የሀገር ልጆችን በኩራት እናስታውሳለን ብለዋል
አረብ ኢምሬትስ በየዓመቱ ህዳር 21 ቀን የተሰው ልጆቿን ትዘክራለች።
በበዓሉ የልጆቿን ጀግንነት በማስታወስ ለሀገራቸው ህይወታቸውን አሳልፈው በመስጠታቸው ተወድሰዋል።
ኤምሬቶች የመቻቻልና የሰላም ምልክት ሆኖ እንዲቀጥል ህይወታቸውን በሀገር ወዳድነትና በታማኝነት መስጠታቸው ትርጉሞች አለው ተብሏል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ቢን አል ናህያን መስዋዕት የሆኑ የሀገራችን ጀግኖችን ያመሰገኑ ሲሆን የድፍረት እሴቶችን ይዘው ያደረጉትን ጉዞ ጠቅሰዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነህያን በዓሉን አስመልከተው በትዊተር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት፡ "በሰማዕታት ቀን ለኤምሬቶች ክብርና ኩራት ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው ሰጥተው ስማቸውን በደመቀ የክብሩ ገፆች ላይ ያሰፈሩ ልጆቻችንን በኩራት፣ በአመስጋኝነት እና በታማኝነት እናስታውሳለን" ብለዋል።
"ሰማዕታት የከፈሉት መስዋዕትነት በታሪክ ውስጥ የህዝባችንን ትክክለኛ እሴት ያቀፈ ነው" ሲሉም አክለዋል።
አረብ ኢምሬትስ የሰማዕታት ቤተሰቦች የድጋፍ እና እንክብካቤ ለማድግ መርሀ-ግብር ቀርጻ እየሰራች እንደሆነ ተናግራለች።
"የሰማዕታት ቀን" በሲቪል ፣ በወታደራዊ እና በሰብዓዊ አገልግሎቶች ህይወታቸውን ላበረከቱት ሰማዕታት መስዋዕትነት እና ትጋት እውቅና በመስጠት የሚከበር በዓል ነው።
ቀኑ በየዓመቱ በፈረንጆቹ ህዳር 30 ቀን የሚከበር ሲሆን በማግስቱ ደግሞ አረብ ኢምሬትስ ብሄራዊ በዓሏን ታከብራለች።