የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ በኦማን ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው
ኢምሬትስ እና ኦማን በየኢነርጂ እና የኢንዱስትሪ መስኮች 16 የትበብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል።
የኦማን ሱልጣኔት እና አረብ ኢሚሬትስ 16 ስምምነቶችን እና የመግባቢያ ሰነዶችን በተለያዩ መስኮች በተለይም በኢነርጂ እና በኢንዱስትሪ ተፈራርመዋል።
በኦማን ዋና ከተማ ሙስካት በአል አላም ቤተ መንግስት የተፈረሙት ስምምነቶችም የትራንስፖርት፣ የመገናኛ እና የሎጂስቲክስ መስኮች፣ የባህር ትራንስፖርት ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ መስኮች ትብብር እና ኢንቨስትመንትን ያካትታሉ ተብሏል።
ሁለቱ ሀገራት በባህልና ወጣቶች፣ በግብርና፣ በእንስሳትና በአሳ ሀብት፣ በምግብ ደህንነት፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ በሳይንሳዊ ምርምር፣ በፈጠራና በሙያ ስልጠናዎች የትብብር ሰምምነት አድርገዋል።
በስምምነቶቹ ውስጥ የትብብር መስኮች ዜና እና የመረጃ ልውውጥ እና የገንዘብ ዝውውር እና ተዛማጅ ወንጀሎችን እና አሸባሪዎችን የገንዘብ ድጋፍን በተመለከተ የመረጃ ልውውጥን ያካትታሉ።
በኦማን የባቡር ሀዲድ እና በኢትሃድ ባቡር እና በኦማን ኮሙዩኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቡድን "የኢንተለጀንስ ቡድን" መካከል በትብብር መስክም ስምምነቶች ተፈርመዋል።
በተጨማሪም በሙስካት የአክሲዮን ልውውጥ እና በአቡ ዳቢ ሴኩሪቲስ ልውውጥ፣ የርቀት የድለላ ኩባንያዎችን የርቀት ግብይት በኤሌክትሮኒካዊ ግብይት ለመተባባር ተስማምተዋል።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ከትናንት ጀምሮ በኦማን ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።
ኦማን ለአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ የሀገሪቱን ከፍተኛ ኒሻን ሸልማለች።