አረብ ኢምሬትስ እና አሜሪካ በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው ትብብር
ሁለቱ ሀገራት ያደረጉት ትብብር የዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችግሮችን ለመፍታት አለምአቀፍ ትብብር ጠቃሚ መሆኑን ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል

የሁለቱ ሀገራት ነዳጅ ያልሆነ የንግድ ልውውጥ 40 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል
አረብ ኢምሬትስ እና አሜሪካ በዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው ትብብር
አረብ ኢምሬትስና አሜሪካ በአርቴፊሻል በኢንተሊጀንስ(ኤአይ) ዘርፍ የሚያደርጉት ትብብር ፈጠራና የቴክኖሎጂን ለማሻሻል ቀዳሚ ሞዴል ነው ተብሏል።
አረብ ኢምሬትስ ከአሜሪካ ጋር በመሆን በኤአይና በቴክኖሎጂ ጥራት ለውጥ እንዲመጣ ትሻለች። ሁለቱ ሀገራት ያደረጉት ትብብር የዘመናዊ የቴክኖሎጂ ችግሮችን ለመፍታት አለምአቀፍ ትብብር ጠቃሚ መሆኑን ማሳያ ነው።
የስነምግባር እሴቶች ለመጠበቅ እና በኃላፊነት ለመጠቀም ያላቸውን ቁርጠኝነት የገለጹት ሁለት ሀገራት በትብብር አለምን የሚጠቅም ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ እድገት ለማሳካት ይፈልጋሉ።
የዱባይ ምክትል ገዥና የአረብ ኢምሬትስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አልናህያን ትናንት ወደ አሜሪካ ያቀኑ ሲሆን በኋይትሀውስ ከከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣናት ይወያያሉ ተብሏል። በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩበት ሁኔታ እና በርካታ አስርት አመታት ያስቆጠረውን ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ዋም ዘግቧል።
የሁለቱ ሀገራት ነዳጅ ያልሆነ የንግድ ልውውጣቸው 40 ቢሊዮን ገደማ የደረሰ ሲሆን የሸቀጦች ንግድ ደግሞ በ9.47 በመቶ አድጎ በ2024 34.43 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ይህ በ2023 ከነበረው 31.45 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ አሳይቷል።
አረብ ኢምሬትስ ከ2018-2023 በአሜሪካ ያደረገችው ኢንቨስትመንት 3.7 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን አሜሪካ በተመሳሳይ ወቅት በአረብ ኢምሬትስ 9.5 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት አድርጋለች።