የአረብ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሪያድ በጋዛ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ
የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀጣናው ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በጋዛ ጉዳይ በሪያድ ተወያይተዋል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ እና ሙሉ ተኩስ አቁም መደረግ እንዳበት በአጽንኦት ተናግረዋል ተብሏል
የአረብ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሪያድ በጋዛ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ።
የአረብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቀጣናው ጉብኝት ካደረጉ በኋላ በጋዛ ጉዳይ በሪያድ ተወያይተዋል።
በርካታ የአረብ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋዛ እየተካሄደ ባለው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ጉዳይ መወያየታቸውን ሮይተርስ የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ሚዲያን ጠቅሶ ዘግቧል።
የብሊንከን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ያስችላል የሚል ተስፋ ፈጥሮ ነበር።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ባለፈው ረቡዕ ሀማስ በተኩስ አቁም እና ታጋቾች መልቀቅን በተመለከተ ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ ውድቅ አድርገዋል። ነገርግን ብሊንከን አሁንም ቢሆን ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በሳኡዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ንጉስ ፌይሰል ቢን ፋርሃን ጠሪነት የተካሄደው የትናንትናው ስብሰባ የግብጽን፣ የኳታርን፣ የጆርዳንን እና የአረብ ኢምሬትስን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የፍልስጤም ሊብሬሽን ኦርጋናይዜሽን(ፒኤልኦ) ዋና ጸኃፊን ያሳተፈ ነበር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አስቸኳይ እና ሙሉ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና 'የቱ ስቴት ሶሉሽን' ትግበራ ሂደት የማይቀለበስበት ደረጃ መድረስ እንዳበት በአጽንኦት ተናግረዋል ተብሏል።
አራት ወራት ያስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እንዳቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ያስችላል የተባለ በምዕራፍ የተከፋፈለ የተኩስ አቁም ሀሳብ ቀርቧል።
በቀረበው ሀሳብ ላይ ሁለቱ ወገኖች በቅደም ሁኔታዎቹ ላይ ልዩነት አንጸባርቀዋል።
አደራዳሪዎቹ ኳታር፣ግብጽ እና አሜሪካ በሁለቱ አካላት መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለማጥበብ እየሰሩ መሆናቸውን ኤፒ ዘግቧል።