እስራኤል እና ሀማስ ያልተስማሙባቸው ነጥቦች ምንድናቸው?
አራት ወራት ያስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እንዳቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ያስችላል የተባለ በምዕራፍ የተከፋፈለ የተኩስ አቁም ሀሳብ ቀርቧል
አደራዳሪዎቹ ኳታር፣ግብጽ እና አሜሪካ በሁለቱ አካላት መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለማጥበብ እየሰሩ ናቸው ተብሏል
እስራኤል እና ሀማስ ተኩስ በማቆም እና ታጋቾችን በመልቀቅ ጉዳይ ምን ያህል ተራርቀዋል?፣እስራኤል እና ሀማስ ያልተስማሙባቸው ነጥቦች ምንድናቸው?
አራት ወራት ያስቆጠረው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እንዲቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ያስችላል የተባለ በምዕራፍ የተከፋፈለ የተኩስ አቁም ሀሳብ ቀርቧል።እስራኤል እና ሀማሰ ይህን ምክረ ሀሳብ አየመረመሩት ይገኛሉ።
ሁለቱ ወገኖች በቅደም ሁኔታዎቹ ላይ ልዩነት አላቸው።
አደራዳሪዎቹ ኳታር፣ግብጽ እና አሜሪካ በሁለቱ አካላት መካከል ያሉትን ልዩነቶች ለማጥበብ እየሰሩ መሆናቸውን ኤፒ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ሁለቱ አካላት ያልተስማሙባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
እስራኤል፦ ሀማስ ከስልጣን እንዲወገድ ትፈልጋለች
ሀማስ፦ ጋዛን ተቆጣጥሮ እያስተዳደረ መቀጠል ይፈልጋል
ያልተስማሙበት ነጥብ፦ የሀማስን የወታደራዊ እና የማስዳደር አቅሙን ጨርሶ ማጥፋት እስራኤል እያካሄደች ያለው ዘመቻ ዋነኛ ግብ ነው።
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት ጥቅምት ወር ሀማስ በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ እና ከባድ የተባለ ጥቃት በማድረስ 1200 ሰዎችን ገድሎ እና 250 ሰዎችን ማገቱን ተከትሎ ነበር እስራኤል በአጸፋ የሀማስ ይዞታ በሆነችው ጋዛ ላይ ጥቃት የከፈተችው። እስራኤል ይህ ቡድን ሌላ ጥቃት እንዳያደርስ ሆኖ መመታት አለበት የሚል እምነት አላት።እስራኤል የጋዛን የጸጥታ ሁኔታም መቆጣጠር ትፈልጋለች።
ሀማስ፦ በእስራኤል የታሰሩ ከፍተኛ የፍልስጤም ታጣቂዎች እንዲፈቱ ይፈልጋል።
እስራኤል፦ እነዚህን ታጣቂዎች መፍታት አትፈልግም
ያልተስማሙበት ነጥብ፦ በከባድ ወይም በቀላል ወንጀል የተከሰሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከረጅም ጋዜው ግጭተ ጋር በተያያዘ በእስራኤል ታስረው ይገኛሉ።
ከዚህ በፊት እስራኤል የተያዙባትን ለማስለቀቅ ፍልስጤማውንን ከእስር የለቀቀችበት ጊዜ ነበር።
በ2011 እስራኤል አንድ በሀማስ የተየዘ ወታደሯን ለማስለቀቅ 1027 ፍልስጤማውያን እስረኞችን መልቀቋ ይታወሳል።
ከተለቀቁት መካከል የጥቅምቱን ጥቃት አቀነባብሯል የሚባለው የሀማስ የአሁኑ መሪ የህያ ሲንዋር ይገኝበታል።
ሀማስ በመቶዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲለቀቁ ይፈልጋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒሰትር ኔታንያሁ እና የቀኝ ዘመም አጋሮቻቸው የሀማስ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እንዲለቀቁ አይፈልጉም።
ሀማስ ያቀረበውን ብዛት ያላቸው እስረኞችን የመልቀቅ ጥያቄ ላይቀበሉት የሚችሉበት ሰፊ እድል አለ ተብሏል።
እስራኤል፦ ታጋቾቹ ከተለቀቁ በኋላ ጦርነቱን መቀጠል ይፈልጋሉ
ሀማስ፦ ታጋቾች ከተለቀቁ በኋላ ጦርነቱ በዘላቂነት እንዲቆም ይፈልጋል
ያልተስማሙበት ነጥብ፦ ኔታንያሁ እስራኤል በሀማስ ላይ ሙሉ ድል እስከምታገኝ ድረስ ጦርነቱን ትቀጥላለች ብለዋል። እስራኤል ጦሯ በጋዛ እንዲቆይ እና ሀማስን እንዲያጠፋ ትፈልጋለች።
ሀማስ ግን ታጋቾችን ለመልቀቅ መደራደር ከመጀመሩ በፊት እስራኤል ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም ቁርጠኛ መሆን አለባት ብሏል።