ግብጽ ያቀረበችው ጋዛን የተመለከተው እቅድ ድጋፍ አገኘ
አረቦች ያቀረቡት የጋዛ እቅድ ጋዛን የመካከለኛው ምስራቅ ውብ ቦታ አደርጋለሁ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የሚፎካከር ነው

እስራኤል የመጀመሪያ ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲራዘም የጠየቀች ሲሆን ሀማስ በበኩሉ ሁለተኛው ዙር ድርድር እንዲጀመር ይፈልጋል
ግብጽ ያቀረበችው ጋዛን የተመለከተው እቅድ ድጋፍ አገኘ።
የአረብ ጉባኤ ረቂቅ መግለጫ ግብጽ ያቀረበችውን የጋዛ እቅድ ማጽደቁንና አለምአቀፉ ማህበረሰብና የፋይናንስ ተቋማት እቅዱን በፍጥነት እንዲደግፉት ጥሪ አቅርቧል።
አረቦች ያቀረቡት የጋዛ እቅድ ጋዛን የመካከለኛው ምስራቅ ውብ ቦታ አደርጋለሁ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡትን የሚፎካከር ነው።
ፕሬዝደንት ትራምፕ ባልተጠበቀ ሁኔታ አሜሪካ ጋዛን በቁጥጥሯ ስር እንደምታደርግ፣ 2.2 ሚሊዮን ገደማ ነዋሪዎቿን ወደ ሌላ ሀገር እንደምታዛውርና "የመካከለኛው ምስራቅ ውብ ቦታ" እንደምታደጋት መናገራቸው የአረቡን አለም አበሳጭቷል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ የአረብ ሀገራት በተለይም ግብጽና ጆርዳን 16 ወራት በዘለቀው የእስራኤል-ሀማስ ጦርነት የወደመችው ጋዛ እስከምትጸዳና መልሳ እስከምትገነባ በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን እንዲያስጠልሏቸው ጫና ሲያደርጉ ቆይተወዋል።
ነገርግን የአረብ ሀገራት ትራምፕ ያቀረቡትን ሀሳብ በጽኑ ተቃውመውታል።
ሀገራቱ ፍልስጤማውያን ከቦታቸው ሳይፈናቀሉ የመልሶ ግንባታው አካል መሆኑን ይጠባቸዋል ብለዋል።
እስራኤል-ሀማስ ባለፈው ጥር ወር መጨረሻ የደረሱት 33 የእስራኤል ታጋቾች በ2000 ገደማ የፍልስጤም እስረኞች ተለውጠው እንዲለቀቁ ያስቻለው የመጀመሪያው ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ባለፈው ቅዳሜ ተጠናቋል።
ይህን ተከትሎ እስራኤል የመጀመሪያ ዙር ተኩስ አቁም ስምምነት እንዲራዘም የጠየቀች ሲሆን ሀማስ በበኩሉ ዘላቂ ተኩስ አቁምና የእስራኤል ከጋዛ መውጣት ጉዳዮች ይነሱበታል የተባለው ሁለተኛው ዙር ድርድር እንዲጀመር ይፈልጋል።