
ጥሩ ውጤት አምጥተሸል ተብላ የስኮላርሽፕ እድል የተሰጣት ይህች ተማሪ ከክፍል ጓደኞቿ ጋር የተራራቀ እውቀት መያዟን ተከትሎ የቀድሞ ትምህር ቤቷን ከሳለች
ከነ መሀይምነቴ አስመርቆኛል ያለችውን ትምህርት ቤት የከሰሰችው ተማሪ
አሌይሻ ኦርቲዝ የተባለችው የ19 ዓመት ተማሪ ከአንድ ዓመት በፊት ነበር የሁለተኛ ደረጃ ትምህረቷን በከፍተኛ ውጤት አጠናቃለች የተባለችው፡፡
በአሜሪካዋ ኮኔክቲከት ግዛት ባለ ትምህርት ቤት ትምህርቷን የተከታተለችው ይህች ተማሪ ከፍተኛ ውጡት ማምጣቷን ተከትሎ የስኮላርሽፕ እድል ተመቻችቶላት በመማር ላይ ነበረች፡፡
ይሁንና የተማሪ አሌይሻ መጻፍ፣ ማንበብ እና ተያያዥ ክህሎት አብረዋት ከሚማሩት ተማሪዎች በብዙ እጥፍ ወደኋላ እንደቀረች ትረዳለች፡፡
ከክፍል ጓደኞቿ ጋር እኩል መጓዝ ያልቻለችው ተማሪዋ ትምህርቷን ለማቋረጥ መገደዷን ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቧል፡፡
እኔ መሀይም ሆኛ ሳለ ትምህርት ቤቴ ግን በከፍተኛ ማዕረግ ብሎ ማስመረቁ ትክክል አይደለም ያለችው አሌይሻ የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ላይ ክስ መመስረቷን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ተማሪዋ አሁን ላይ ያላት እውቀት አንደኛ ክፍል ካለ ተማሪ ጋር ተመሳሳይ ነው የተባለ ሲሆን እርሳስ መያዝ እና የተወሰኑ ቃትን ብቻ ማንበብ ትችላለችም ተብሏል፡፡
መሀይም ሆነሽ ሳለ እንዴት ኮኔክትከት ዩንቨርሲቲን እንዴት ተቀላቀልሽ በሚል ለቀረበላት ጥያቄም ማመልከቻዎቹን ለመሙላት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እና የትርጉም መተግበሪያዎችን ተጠቅማ እንደነበር ተናግራለች፡፡
አሁን ላይ ከዚህ በላይ መታገል እንደማልችል እና ለደረሰብኝ የዐዕምሮ ህመም ህክምናዎችን ከወሰድኩ በኋላ ወደ ትምህርቷ ልትመለስ እንደምትችልም አክላለች፡፡
የትምህርት ቤቱ አማራሮች በግዴለሽነት በእኔ ላይ ላደረጉት ጥፋት መቀጣት አለባቸው የምትለው ተማሪዋ ሌሎች ተማሪዎች መሰል ጉዳት እንዳይደርስባቸው በሚል ክስ መመስረቷ ተገልጿል፡፡