ሩሲያ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቋረጧን አወደሰች
ክሬምሊን አሜሪካ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቆሟ ለሰላም የተሻለ ተስፋ የሚሰጥ ነው ብሏል

ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠው ወታራዊ ድጋፍ እንዲቋረጥ አዘዋል
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማቋረጣቸውን ተከትሎ ሩሲያ እርጃውን አወድሳለች።
ክሬምሊን በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ “አሜሪካ የጦር መሳሪያ አቅርቦቱን ማቆሟ ለሰላም መንገድ የሚከፍት ነው” ያለ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የወሰዱት እርምጃ ዝርዝር ሁኔታ ግልጽ መደረግ እንዳለባት አሳስቧል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ ለዩክሬን የሚደገውን ወታደራዊ ድጋፍ ማቋረጣቸውን ዋይት ኃውስ ማስታወቁ ተገልጿል።
አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው እርዳታ ለሰላም ለመፍትሄው አስተዋጵኦ ማበርከቱን ለማረጋገጥ አቋርጠን እየገመገምን ነው" ሲሉ የዋይት ኃውስ ባለስልጣን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህንንተከትሎም የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የአሜሪካ ዕርዳታ መቆሙን ሩሲያ እንደምትቀበለው ገልጸው፤ ነገር ግን እና ዝርዝሮቹ መታየት አለባቸው ብለዋል ።
ዲሚትሪ ፔስኮቭ አክለውም አሜሪካ እርዳታውን ማቆሟ እውን ከሆነ የኪቭ መንግስት ወደ ሰላም ሂደቱ እንዲመጣ የሚያበረታታ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
አሜሪካ ለጡርነቱ ከፍኛ የመሳሪያ አቅራ እደሆነች ግልጽ ነው ያሉት ፔስኮቭ፤ አሜሪካ አቅርቦቷን ካቋረጠች ለሰላ መስፈን ትልቁን ሚና ሊጫወት እንደሚችልም አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን ሰላም እንዲሰፍን ያላቸውን ምኞት አስመልክቶ የሰጡትን መግለጫ ሩሲያ በደስታ ተቀብላለች ብለዋል ፔስኮቭ።