ለግጭት ብቸኛው መፍትሄ 'ቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ የአረብ ሀገራት እና የአውሮፖ ህብረት ተስማሙ
'ቱ ስቴት ሶለሽን' ዌስትባንክን እና ጋዛን ያካተተ የፍልስጤም መንግስት ከእስራኤል ጎን ለጎን እንዲመሰረት የሚያስችል ስምምነት ነው
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች የነበረው መጠነሰፊ ጥቃት በኳታር አደራዳሪነት በተደረሰ ተኩስ አቁም በጊዜያዊነት ቆሟል
ለግጭት ብቸኛው መፍትሄ 'ቱ ስቴት ሶሉሽን' ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ የአረብ ሀገራት እና የአውሮፖ ህብረት ተስማሙ።
የእስራኤል እና የፍልስጤም ግጭት የሚቆመው 'ቱ ስቴት ሶሉሽንስ' ወይንም የሁለት መንግስታት መፍትሄ ተግባራዊ ሲደረግ መሆኑን የአረብ ሀገራት ባለስልጣናት እና የአውሮፖ ህብረት በትናንትናው እለት ተስማምተዋል።
ጋዛን ከሀማስ ይልቅ የፍልስጤም ባለስልጣን ሊያስተዳድሯት እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአውሮፖ ህብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በስፔን ባርሴሎና በተካሄደው ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ሁሉም የተሳተፉት የህብረቱ አባላት እና ሌሎቹም 'ቱ ስቴት ሶሉሽን' እንደሚያስፈልግ ተስማምተዋል።
የፍልስጤም ባለስልጣን ምርጫ ማድረግ እና አስተዳዳሩን ማሻሻል አለበት ያሉት ቦሬል በጋዛ የሚፈጠረውንም የስልጣን ክፍተት መሙላት ይጠበቅበታል ብለዋል።
የጆርዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ የፍልስጤም ህዝብ ማን እንዲመራው እንዲሚፈልግ መወሰን እንዳለበት እና ጋዛ እና ዌስትባንክ እንደአንድ አካል መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
'ቱ ስቴት ሶለሽን' ዌስትባንክን እና ጋዛን ያካተተ የፍልስጤም መንግስት ከእስራኤል ጎን ለጎን እንዲመሰረት የሚያስችል ስምምነት ነው።
የፍለስጤም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪያድ አል ማሊኪ በ2007 ከሀማስ ጋር በተደረገ የስልጣን ሽኩቻ ጋዛን የማስተዳደር ስልጣኑን ያጣው የፍልስጤም ባለስልጣን ወደ ጋዛ መመለስ አያስፈልግም ብለዋል።
"ሁልጊዜም እዛው አለን። 60ሺ የመንግስት ሰራተኞች አሉን"።
እስራኤል የአውሮፖ ህብረት እና የአረብ ሀገራት በተሳተፉበት ስብሰባ አልተገኘችም።
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደች የነበረው መጠነሰፊ ጥቃት በኳታር አደራዳሪነት በተደረሰ ተኩስ አቁም በጊዜያዊነት ቆሟል።
በተደረሰው ተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት ሀማስ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች