እስራኤል በስፔን ላይ ቁጣዋን አሰማች
ሳንቼዝ "በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶችን እና ሴቶችን ጨምሮ በንጹሃን ላይ የሚደረገው ግድያ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ሽብርተኝነት የሚያበረተታ ነው ስትል እስራኤል ቁጣ ያዘለ ምላሽ ሰጥታለች
እስራኤል በስፔን ላይ ቁጣዋን አሰማች።
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስቴር ፔድሮ ሳንቼዝ ባለፈው አርብ በጋዛ ድንበር ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ አድርሳዋለች ያሉትን "ጅምላ ግድያ" ማውገዛቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ሽብርተኝነት የሚያበረተታ ነው ስትል እስራኤል ቁጣ ያዘለ ምላሽ ሰጥታለች።
ግብጽ በምትቆጣጠረው የራፋህ ማቋረጫ ከቤልጀም ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዲ ካሮ ጋር የነበሩት ሳንቼዝ ፍልስጤማውያን ከገቡበት የህይወት ምስቅልቅል እንዲወጡ ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቅርዋል።
ሳንቼዝ "በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶችን እና ሴቶችን ጨምሮ በንጹሃን ላይ የሚደረገው ግድያ ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።
የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢሊ ኮኸን ባወጡት መግለጫ ሳንቼዝ እና ዲ ካሮ ሀሰት በመናገር ሽብርተኝነትን አበረታተዋል የሚል ክስ አቅርዋል።
ሚኒስትሩ ሁኔታውን እንዲያብራሩ የስፔንን እና የቤልጀምን አምባሳደሮች መጥራታቸውን ገልጸዋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ሁለቱ የአውሮፖ ሀገራት የፍልስጤሙ ሀማስ በሰብአዊነት ላይ የፈጸመውን ወንጀል ለመናገር አልደፈሩም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር ጥቃት በፈጸመበት ወቅት አግቶ ከወሰዳቸው 240 ታጋቾች ውስጥ በኳታር አደራዳሪነት በተደረሰው ስምምነት 24ቱን በትናንትናው እለት ለቋል።
እስራኤልም በተመሳሳይ 50 የሚሆኑ የፍልስጤም እስረኞችን ለቃለች።
ተኩስን ጋብ ለማድረግ የተስማማችው እስራኤል ሀማስን ሳታጠፋ ተኩስ እንደማታቆም መግለጿ ይታወሳል።