በእስራኤል ሃማስ ተኩስ አቁም ስምምነት እስካሁን ምን ያክል የታጋችና እስረኛ ልውውጥ ተደረገ?
የአራት ቀን የተኩስ አቅም ስምምነትን ተከትሎ ሃማስ ከአርብ ጀምሮ ታጋቾችን እየለቀቀ ነው
እስራኤል በተኩስ አቁም ስምምነቱ መሰረት ፍሊስጤማውያን እስረኞችን እየፈታች ነው
እስራኤልና ሃማስ በጋዛ ለአራት ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ የደረሱት ስምምነት አርብ ጠዋት ላይ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወቃል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዛሬ 3ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ ለአራት ቀናት በሚቆየው ስምምነቱ ሃማስ 50 ታጋቾችን እንደሚለቅ፤ በአንጻሩ እስራኤል ደግሞ 150 እሰረኞችን እንደምትለቅ ይጠበቃል።
በተኩስ አቁም እምምነቱ መሰረት እስካሁን 26 የእስራኤል ዜጎች፣ 78 ፍሊስጤማውያን፣ 14 የታይላንድ ዜጎችና አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ ከእገታና ከእስር ተለቀዋል።
በ3ኛ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስካሁን ምን ተካሄደ፤ ምንስ ይጠበቃል?
ባሳለፍነው አርብ ሃማስ 13 የእስራኤል ዜጎችን የለቀቀ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ህጻናትና ሴቶች ናቸው ተብሏል።
እስራኤልም አርብ እለት 39 የፍሊስጤም ዜጎችን የለቀቀች ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ ህጻናትና ሴቶች ናቸው
ሃማስ ዛሬ እሁድ ሃማስ 13 እስራኤላውያን ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን፤ ከእነዚህም 6 ሴቶችና 7 ህጻትና ታዳጊዎች ናቸው።
እስራኤልም በዛሬው እለት 39 ፍሊስጤማውያንን የለቀቀች ሲሆን፤ 6 ሴቶችና 33 ህጻትና ታዳጊዎች ናቸው።
የ4 ቀን የተኩስ አቁም ከተጀመረ ወዲህ ሃማስ 14 የታይላንድ ዜጎችና አንድ የፍሊፒንስ ዜጋ ከእገታና መልቀቁም ተነግሯል።
በዛሬው እለትም ተጨማሪ የእስራኤል ዜጎች ከእገታ እንደሚለቀቁ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ሃማስ የሚለቃቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ለእስራኤል መላኩ ተነግሯል።
እስራኤል አሁንም 195 ሰዎች በማሃመስ ታግተው እንደሚገኙ ተናግራለች።
የጋዛ ነዋሪዎች በተኩ አቁሙ ወቅት መሰረታዊ የሆኑ እንደ ነዳጅ፣ ምግብ እና መድሃኒት ያሉ መሰረታዊ ፍጆታዎችን ለሟሟላት እየተሯሯጡ ነው።
ሃማስ በፈረንጆቹ ጥቅምት 7 በእስራኤል ላይ በወሰደው ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ ጥቃት 1 ሺህ 200 ሰዎች እስራኤላውያን የሞቱ ሲሆን፤ 240 ሰዎች ደግሞ መታገታቸው ይታወሳል።
በእስራኤል የአጸፋ እርምጃ ከ14 ሺህ 500 በላይ ፍሊስጤማውያን መሞታቸውን ጋዛን የሚያስተዳደርረው የሃማስ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።