አርጀንቲና በመጭው እሁድ በፍሎሪዳ በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ኡሯጓይን ወይንም ኮሎምቢያን ትገጥማልች
የሊዮነል ሜሲዋ አርጀንቲና ለኮፓ አሜሪካው የፍጻሜ ውድድር አለፈች።
በትናንትናው እለት በአሜሪካ ኒው ጀርሲ በተካሄደው የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጁሊያን አልቫሬዝ እና ሊዮነል ሜሲ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች አማካኝነት አርጀንቲና ካናዳን 2-0 በማሸኘፍ ለዋንጫ ውድድር ማለፍ ችላለች።
አርጀንቲና በመጭው እሁድ በፍሎሪዳ በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ኡሯጓይን ወይንም ኮሎምቢያን ትገጥማልች። በዚህ ጨዋታ ሜሲን፣ አንግል ዲማሪያን እና ኒኮላስ ኦተመንዲን ጨምሮ በርካታ የአርጀንቲና ኮከቦች ይሳተፉበታል።
"እንደብሄራዊ ቡድን ባገኘነው ድል እየተደሰትን ነው። በድጋሚ የዋንጫ አሸናፊ ለመሆን ለፉጻሜ ጨዋታ መድረስ ቀላል አይደለም" ሲል ሜሲ ቲዋይሲ ስፓርት ተናግሯል።
አርጀንቲኒ 15 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫዎችን ያነሳች ሲሆን ስድስት ጊዜ ደግሞ ለዋንጫ ፍልሚያ ቀርባለች።
በዚህ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ፣ ካናዳ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ጫና ፈጥራ የነበረ ቢሆንም አልቫሬዝ ሁለት ተከላካዮችን አልፎ በ22ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል አርጀንቲናን መሪ አድርጋለች።
በኳታር አስተናጋጅነት የተዘጋጀው የ2022 የዓለም ዋንጫ አሸናፊ እና በፊፋ የእግርኳስ ደረጃ አንደኛ ላይ የምትገኘው አርጀንቲና፣ ጨዋታውን ቀስበቀስ በመቆጣጠሯ ሜሲ በ44ኛው ደቂቃ ግብ የማስቆጠር እድል አግኝቶ ነበር።
የካናዳው ጆናታን ዴቪል አቻነት ጎል ለማስቆጠር እድል አግኝቶ የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ርቀት ላይ የመታው ምት በግብ ጠባቂው ኢሚሊያኖ ማርቲኔዝ ከሽፏል።
ሜሲ በውድድሩ መጀመሪያ አካባቢ በጡንቻ ህመም ሲሰቃይ ነበር፤ ነገርግን ከፍተኛ ወበቅ በነበረበት የሜትላይፍ ስቴዲየም በሙሉ አቅሙ በመንቀሳቀስ በ51ኛው ደቂቃ ለአርጀንቲና ሁለተኛውን ግብ አስቆጥሯል።
ካናዳ ሽንፈት ቢገጥማትም፣ የተሻለ ግምት ከተሰጣቸው እና የ2026 የአለም ዋንጫ አሸናፊ ከሆኑት የኮፓ አሜሪካ ውድድር ተቀናቃኞቿ ሜክሲኮ እና አሜሪካ የተሻለ ውጤት አስመዝግባለች።