ሜሲ በሆንግ ኮንግ ጨዋታ ሳይሰለፍ የቀረበትን ምክንያት ግልጽ አደረገ
አድናቂዎቹ ሜሲ ከሶስት ቀናት በኋላ በቶኪዮ የወዳጅነት ጨዋታ ሲታይ ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል
በሆንግ ኮንጉ ጨዋታ ያልተሳተፈው በፖለቲካዊ እና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ነው የሚሉ ሰዎችን እየሰማ መሆኑን የገለጸው ሜሺ "ያ ፍጹም እውነት ያልሆነ ነው" ብሏል
ሊዮነል ሜሲ ኢንተር ሚያሚ በሆንግ ኮንግ ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ካለመሰለፉ ጋር ተያይዞ የሚነሱ አሉባልታዎችን በተመለከተ የቻይናውን ትልቁን ማህበራዊ ሚዲያ ዌቦን በመጠቀም ግልጽ አድርጓል።
የቻይና መንግስት ሚዲያዎች፣ የሆንግ ኮንግ ፖለቲከኞች፣ እና አድናቂዎች የ36 አመቱ አርጀንቲናዊ አጥቂ ከሶስት ቀናት በኋላ በቶኪዮ የወዳጅነት ጨዋታ ሲታይ ቁጣቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
በዚህ ምክንያት ሀንግዙ እና ቤጂንግ በመጋቢት እንደሚካሄዱ መርሃግብር የወጣላቸውን የአርጀንቲና ጨዋታዎች እንደማያስተናግዱ ሲገልጹ ቆይተዋል። ሜሲ ይህን ሁኔታ ለማርገብ በማሰብ ሳይሰለፍ የቀረው በፖለቲካዊ ምክንያት አለመሆኑን ተናግሯል።
"ከሆንግ ኮንጉ ጨዋታ በኋላ ብዙ ነገሮችን እያነበብኩ እና እየሰማሁ ነው። ማንም ሰው የውሸት ታሪኮችን እንዳይሰማ እና እውነታውን እንዲያውቅ ይህን ቪዲዮ ሪከርድ አድርጌ ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ" ሲል በዌቦ ላይ በፖሰተው ቪዲዮ ተናግሯል።
በሆንግ ኮንጉ ጨዋታ ያልተሳተፈው በፖለቲካዊ እና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ነው የሚሉ ሰዎችን እየሰማ መሆኑን የገለጸው ሜሺ "ያ ፍጹም እውነት ያልሆነ ነው" ብሏል።
"እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ጃፖንን ወይም ቻይናን ብዙ ጊዜ አልጎበኝም ነበር። መጫወት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ከቻይና ጋር ቅርብ እና ልዩ ግንኙነት አለኝ"
ሜሲ በፈረንጆቹ የካቲት አራት በጉጉት ሲጠበቅ ከነበረው ኢንተር ሚያሚ ከሆንግ ኮንጉ ሊግ ሺ ጋር ባደረገው ጨዋታ ያልተሰለፈበትን ምክንያት በድጋሚ አብራርቷል።
ሜሲ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው እና በመጀመሪያው የሳኡዲ አረቢያ ጨዋታ መጫወት እንዳልቻለ ተናግሯል።
"በሁለተኛው ጨዋታ ትንሽ ለመጫወት ሞከርኩ ግን ባሰብኝ። ከዚህ ከጨዋታው አንድ ሲቀረው( የሆንግ ኮንጉ) ልምምድ ለማድረግ ሞክሬ ነበር።"
"ከጥቂት ቀናት በኋላ እየተሻለኝ ሲመጣ ወደ ቀድሞ አቋሜ መመለስ ስላለብኝ በጃፖን ትንሽ ተጫውቻለሁ" ብሏል ሜሲ።