የኢንዶኔዥያው እግር ኳስ ክለብ የ174 ሰዎችን ህይወት ለቀጠፈው የእግር ኳስ ግርግር ይቅርታ ጠየቀ
ፊፋ፤ የጸጥታ አካላት ግርግሩን ለማስቆም የተጠቀሙ "አስለቃሽ ጋዝ" ተገቢ እንዳልበር ገልጿል
የኢንዶኔዥያ ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶ የሀገሪቱ እግር ኳስ ማህበር ሁሉንም የሊጋ 1 ጨዋታዎች እንዲያቆሙ አዘዋል
የኢንዶኔዥያው አሬማ እግር ኳስ ክለብ ፕሬዝዳንት የ 174 ሰዎችን ህይወት ለቀጠፈው የእግር ኳስ ግርግር ይቅርታ ጠየቁ፡፡
የክለቡ ፕሬዝዳንት ጊላንግ ዊዲያ ፕራማና በቴሌቭዥን መስኮት ባደረጉት በእንባ የታጀበ ንግግር "እኔ የአሬማ እግር ኳስ ፕሬዝዳንት ሆኜ ለተፈጠረው ክስተት ሙሉ ሀላፊነቱን እወስዳለሁ፣ ለተጎጂዎች፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለመላው ኢንዶኔዥያውያን እና ሊጋ 1 ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ" ማለታቸው ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
በኢንዶኔዥያ በምስራቅ ጃካርታ በተደረገው አሬማ እና ፐርሴባያ ሱራባያ ቡድኖች የእግር ኳስ ጨዋታ በተፈጠረ ግርግርና መገፋፋት እና መረጋገጥ የ5 ዓመታ ህጻን ልጅን ጨመሮ 174 ሰዎች ሲሞቱ ከ180 በላይ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ግርግሩ የተፈጠረው በሜዳው የሚጫወተው ክለብ መሸነፉን ተከትሎ የተበሳጩ ደጋፊዎች ወደ ሜደ ዘለው በመግባታቸው ነው።
ግርግሩን ለመቆጣጠርም በስፍራው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ የተኮሱ ሲሆን፤ ይህንን በመሸሽ ላይ በነበሩ ደጋዎች ላይ መረጋገጥ እና መተፋፈን መፈጠሩን የመስራቅ ጃካርታ ፖሊስ አዛዥ አስታውቀዋል።
የኢንዶኔዢያ የመገናኛ ብዙሃን በለቀቁት ምሰል በአሬማ ኤፊ እና ፔርስባያ ሱራባያ የእግር ኳስ ክለቦች መካከል መካከል በተደረገ ጨዋታ ላይ መሆኑን የፀጥታ አካላት አስለቃሽ ጭሶችን ወደ ሰማይ ሲቱክሱ ያሳያል።
የዓለም አቀፉ የአግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በጸጥታ አካላት በእግር ኳስ ጨዋታዎች ላይ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ወይም " አስለቃሽ ጋዝ" መጠቀም እንዳልነበረባቸው ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢንዶኔዥያ መንግስት የተፈጠረውን ግርግርን የተመለከተ ተገቢውን ምርመራ የሚያካሂድ ገለልተኛ ቡድን ማቋቋሙ አስታውቋል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጆኮ ዊዶዶ ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ የእግር ኳስ ማህበሩ ሁሉንም የሊጋ 1 ጨዋታዎች እንዲያቆም ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
እንደፈረንጆቹ በ 1964 ፔሩ አርጀንቲናን በሊማ በሚገኘው ስታዲዮ ናሲዮናል ስታስተናግድ 328 ሰዎች የተገደሉበት አጋጣሚ አይዘነጋም፡፡