አርጀንቲናዊው የእግርኳስ ኮከብ ህይወቱ ያለፈው በፈረንጆቹ 2020 በ60 አመቱ ነበር
አርጀንቲናዊው ዲያጎ ማራዶና በዓለም ከታዩ የእግር ኳስ ጠቢቦች በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ አንዱ ነው፡፡
በተለይም ማራዶና በተለይም “የእ/ሔር እጅ” ተብላ በምትታወቀውና እንደፈረንጆቹ 1986 በእንግሊዝ ላይ በእጁ ባስቆጠራት ጎል በርካቶች ያስታውሱታል፡፡
በትናንትናው እለት ማራዶና በእጁ ጎል ሲያስቆጥር ለብሶት የነበረው ማሊያ ፤በእንግሊዝ የመንገድ ልብስ እና የዘመናዊ ስብስቦች ለጨረታ በማቅረብ በሚታወቁት ብርሃን ዋቸር አማካኝ ነት ለጨረታ ቀርቦ በመጀመሪያ ቀኑ በአራት ሚልዮን ፓውንድ መጀመሩም ተገልጸዋል፡፡
ጨረታው በርካታ ሚልዮን ፓውንዶች ሊያወጣ እንደሚችልም ከወዲሁ ተገምቷል፡፡ይሁን እንጂ ለጨረታ የቀረበው ማሊያ “ማራዶና በእንግሊዝ ላይ ጎል ሲያስቆጥር ለብሶት የነበረ ነው ወይስ አይደለም ?” የሚለው፤ ከዲያጎ ማራዶና ቤተሰቦችም ጭምር ጥያቄ እያስነሳ ነው ተብለዋል፡፡
የማራዶና ሴት ልጅ ዳልማ፤ ሜትሮ ለተባለ የአርጀንቲና የሬዲዮ ጣቢያ" ይህ ማሊያ የአባቴ አይደለም፤ ማሊያው ማን ጋር እንዳለ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መናገር አልፈልግም " ማለቷንም ተሰምቷል፡፡
የማራዶና ቤተሰቦች ስለ ማሊያው ጥያቄ ቢያነሱም ፤ አሁን ለጨረታ የቀረበው ማሊያ ላለፉት 19 ዓመታት በእንግሊዝ ብሄራዊ የእግር ኳስ ሙዝየም ውስጥ የነበረ መሆኑ የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ የቀድሞ የናፖሊ እና ቦካ ጁኒየርስ ኮከብ በ60 ዓመቱ ህዳር 2020 ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል፡፡