ስፖርት
የአውሮፓ እግር ኳስ ቡድኖች በወረርሽኙ ምክንያት 8 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገቢ አጥተዋል ተባለ
የስቴዲዬም ገቢ ማጣት እና የስርጭት ክፍያዎች መቀነስ ቡድኖቹን ከገቢ አንጻር እንደጎዳም ነው የተነገረው
ቡድኖቹ ባለፉት 2 ዓመታት ያገኙት የነበረውን 7 ቢሊዮን ዩሮ አጥተዋል ተብሏል
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የአውሮፓ ክለቦችን 8 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ገንዘብ ማሳጣቱን የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር (UEFA) አስታወቀ፡፡
ማህበሩ 2 የውድድር ዓመታትን የተፈታተነው ወረርሽኙ 7 ነጥብ 91 ቢሊዮን ዶላር (7 ቢሊዮን ዩሮ) ማሳጣቱን አስታውቋል፡፡
ኃያል የሚባሉት የአህጉሪቱ ክለቦች በፈረንጆቹ 2021 4 ነጥብ 52 ቢሊዮን ዶላር፤ በ2020 ደግሞ 3 ነጥብ 39 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አጥተዋል፡፡
- ቤልጂዬም ለተከታታይ 4ኛ ጊዜ ቀዳሚ በሆነችበት የፊፋ የሃገራት የእግር ኳስ የደረጃ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ 137ኛ ሆነች
- አርጀንቲናዊው ኮከብ ሰርጂዮ አግዌሮ “በልብ ህምም ምክንያት ራሱን ከእግር ኳስ ማግለሉን” አስታወቀ
በዋናነት ከስቴዲዬም እና ከዝውውር ሊያገኟቸው ይችሉ የነበሩ ገቢዎችን ማጣታቸው እንደጎዳቸውም ነው ማህበሩ ያስታወቀው፡፡
በአህጉሪቱ 54 ሊጎች የሚወዳደሩ የ724 እግር ኳስ ክለቦችን ሁኔታ አጥንነቶ በትንታኔ ያቀረበው የማህበሩ ሪፖርት ከስፖንሰሮች ይገኝ የነበረ 1 ነጥብ 92 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መታጣቱንና ለቴሌቪዥን ስርጭቶች ከተከፈለው ገንዘብ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያህሉ መመለሱን አስቀምጧል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን ተመልካቾች ወደ ስቴዲየሞች በመመለስ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ተስፋ ሰጪ ነገሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡