ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን ለማውረድ የተቃውሞ ሰልፍ እየመሩ ያሉት ሊቀ ጳጳስ
የአርመኑ ሊቀ ጳጳስ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል
አርመን በአዘርቤጃን ወታደራዊ ሽንፈት ከተደረሰባት እና ግዛቷን ካጣች በኋላ የሀገሪቱ ህዝብ ቁጣ ውስጥ ገብቷል
የአርመኑ ሊቀ ጳጳስ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል።
ሊቀ ጳጳሱ ለአራት ቀናት የሚቆየውን እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሽኒያን ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአርመን ዋና ከተማ የርቫን ባስጀመሩበት ወቅት በርካታ ህዝብ ተቃውሞውን ገልጿል።
ሊቀ ጳጳስ ባግራት ጋልስታንያን አርመን በአዘርቤጃን ወታደራዊ ሽንፈት ከተደረሰባት እና ግዛቷን ካጣች በኋላ የተፈጠረውን ቁጣ ተጠቅመው ነው ህዝቡን ለአደባባይ ተቃውሞ የጠሩት።ነገርግን ፓሺኒያን ጫናውን እስካሁን ተቋቁመውት ቆይተዋል።
"ለአራተ ቀናት ያህል በአደባባዮች እና በመንገዶች እንቆያለን፤ በውሳኔያችን እና በፍላጎታችን ድልን እንቀዳጃለን"ያሉት ጋልስታኒያን ፓርላማው ልዩ ስብሰባ አድርጎ መንግስትን ከስልጣን እንዲያነሳው ጠይቀዋል።
በዩቲዩቭ በቀጥታ ሲተላለፍ የነበረው ቪዲዮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በየርቫን ማዕከል ተሰባስበው ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።
ሰልፉን ተከትሎ የተፈጸመ የሰዎች እስርም ይሁን ግጭት የለም።
በፓሺኒያን ላይ ለሳምንታት ሲቀርብ የነበረው ተቃውሞ ከረገበ በኋላ ጋልስታኒያን በቀናት ውስጥ የስልጣን ለውጥ እንዲደረግ የሚጠይቅ ተቃውም በመነሳት ጉዳዩ እንዳይቀዘቅዝ አድርገውታል ተብሏል።
ሊቀ ጳጳሱ በሀገሪቱ እርቅ የሚፈጽም፣ የውጭ ጉዳይን በአግባቡ የሚይዝ እና ምርጫ የሚያዘጋጅ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠይቀዋል።
በየርቫን የሪጂናል ጥናት ማዕከል ዳሬክተር ሪቻርድ ግራጎሲያን ግን የተቃዋሚዎች ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን እና ጥያቄውም ተስፋ መቁረጥ እንደሚታይበት ተናግረዋል።
የሊቀ ጳጳሱ ዘመቻ በፓለቲካ ልምድ የማነስ እና ግልጽ አማራጭ ያለማቅረብ ችግር አጋጥሞታል ብለዋል ዳይሬክተሩ።
በሙያ ጋዜጠኛ የሆኑት ፓሺኒያን ወደ ስልጣን የወጡት በፈረኔጆቹ 2018 የተነሳውን የመንገድ ላይ አመጽ ተከትሎ ነበር።
በሁለተኛው የአርመን- አዘርቤጃን ጦርነት፣ አርመን ሽንፈት ከጋጠማት በኋላ በ2020 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ጫና ገጠማቸው።
አዘርቤጂን ባለፈዉ አመት ባደረሰችው መብረቃዊ ጥቃት አውዛጋቢውን የካራባህ ግዛት መልሳ በመያዝ ለአስርት አመታት በነጻነት ሲኖሩ የነበሩ 100ሺ በላይ አርመኖች ተፈናቅለዋል።