ተመድ በአርመንያ 120 ሺ ስደተኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ አለ
ኮሚሽኑ እስካሁን 88ሺ የሚሆኑ አርመኖች ከናጎርኖ ካራቫህ ወደ አርመንያ መግባታቸውን እና ቁጥሩም ወደ 120ሺ ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል
በናጎርኖ ካራባህ ከሚገኙት አርመኖች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አዘርባጃን በግዛቷ ላይ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ተፈናቅለዋል
የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን ከናጎርኖ ካራባህ የሚፈናቀሉ 120ሺ የአርመን ስደተኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
ኮሚሽኑ እስካሁን 88ሺ የሚሆኑ አርመኖች ከናጎርኖ ካራቫህ ወደ አርመንያ መግባታቸውን እና ቁጥሩም ወደ 120ሺ ሊደርስ እንደሚችል አመልክቷል።
በናጎርኖ ካራባህ ከሚገኙት አርመኖች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አዘርባጃን በግዛቷ ላይ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ ተፈናቅለዋል።
በፍርሃት እና በድካም ስሜት ውስጥ ያሉ ብዙ ሰዎች በመመዝገቢያ ጣቢያዎች መሰብሰባቸውን በአርመንያ የኮሚሽኑ ተወካይ ካቢታ ቤላኒ ተናግረዋል።
"ለወራት ተከበው ነው የቆዩት" ብለዋል ተወካይዋ። "ሲመጡ በሽብር ውስጥ ናቸው፣ ተጨንቀዋል፤ ፈርተዋል መልስም ይፈልጋሉ"
ተሰደው ከሚመጡት ውስጥ 1/3 የሚሆኑት ህጻናት መሆናቸውን የገለጹት የተመድ ኃላፊ ብዙዎቹ ከወላጆቻቸው የተነጠሉ ናቸው ብለዋል።
አርመኖች ለመሰደድ የወሰኑት አዘርጃን ባደረሰችው ጥቃት በግዛቱ ያሉ የአርመን ታጣቂዎች እጁ ከሰጡ እና ትጥቅ ለመፍታት ከተስማሙ በኋላ ነው።
ይህን ተከትሎ የአዘርባጇን አካል መሆን እንደማይፈልጉ የገለጹት አርመኖች ታሪካዊ ነው ወደሚሉት መሬታቸው በመሰደድ ላይ ይገኛሉ።