ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ባወጣችው አዲስ ህግ ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታለች
ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ባወጣችው አዲስ ህግ ምክንያት ከአውሮፓ ህብረት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብታለች
ቤጅንግ የሆንግ ኮንግን ጉዳይ የተመለከተ አዲስ ያዘጋጀችው የጸጥታ ሕግ በአሜሪካና በአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟታል፡፡
“በአንድ ሀገር ሁለት ሥርዓት” ውስጥ ያለችው ሆንግ ኮንግ ከሌሎች የቻይና ግዛቶች የተለየ ነጻነትና አስተዳደር ያላት ሆንግ ኮንግ ከቤጅንግ የወጣላት አዲስ ሕግ ግን ይህንን ነጻነቷን ሊጋፋ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
ግዛቲቱ በርካት የጸጥታ ችግሮች ሲስተዋሉባት እንደነበር የገለጸችው ቤጄንግ ለግዛቲቱ አዲስ የጸጥታ ሕግ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ ሕጉ ሆንግ ኮንግን ከቻይና ስለመገንጠል፣ ሀገር ክህደትንና ሽብርተኝነትን ለመከላከልና ለማውገዝ ያለመ ቢሆንም አሜሪካና አውሮፓ ግን ሆንግ ኮንግን ለማፈን ነው በማለት ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
ቻይና ሕጉ በሆንግ ኮንግ ጉዳይ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመመከት እንደሚያግዛት በማመን በግንቦት በምክር ቤቷ አጽድቃለች፡፡የንብረት፣የኮንትራት፣የግለሰብ መብቶችን፣ጋብቻና ቤተሰብ፣ውርስና የፍትሐ ብሔር ተጠያቂነትን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የያዘው ይህ አዲስ ሕግ ታዲያ ቻይናን ማዕቀብ እንዲጣልባት አድርጓል ነው የተባለው፡፡
የአውሮፓ ሕብረት በዚሁ ቻይና ባወጣችው ሕግ ዙሪያ በቤጅንግ ላይ ማዕቀብ መጣሉን ወል ስትሬት ጆርናል አስነብቧል፡፡ በዚህም መሰረት የአውሮፓ ሕብረት የሆንግ ኮንግ የጸጥታ ሕግ ቻይና እንድትገነባ የሚያስችሉ የቴክኖሎጅ ቁሳቁሶችን ወደ ቻይና ላለመላክ መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በአውሮፓ ሕብረት የሚገኘው የቻይና ተልዕኮም በሕብረቱ ድርጊት ማዘኑን የቻይናው ግሎባል ቴሌቪዥን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሕብረቱ በቻይና የውስጥ ጉዳይ ላይ መግባት እንደሌለበት የገለጸው የቻይናው ተልዕኮ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት የሚችሉት ቻይናውያን በተለይም የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች መሆናቸውንም ነው የገለጸው፡፡
ቻይና በሆንግ ኮንግ ተግባራዊ የሚደረገው ብሔራዊ የጸጥታ ሕግ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ እንዳገዛቸው ስለመግለጻቸው አስታውቃለች፡፡ይሁንና አውሮፓ ሕብረት በቤጅንግ ላይ ማዕቀብ መጣሉን አስታውቋል፡፡ ቻይና በዚህች ልዩ ግዛት ላይ የጣለችው ማዕቀብ አውሮፓና አሜሪካን በተለየ መልኩ ለምን አሳሰባቸው የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ከብራሰልስና ከዋሸንግተን በተጨማሪም አምንስቲ ኢንተርናሽናልም ጉዳዩ የሰው ልጆችን የሰብዓዊ መብት የሚጋፋ ነው እያሉ ነው፡፡
አሜሪካ ቀደም ብላ ከቻይና ጋር የገባችውን የንግድ እሰጥ አገባ በሆንግ ኮንግ በኩል ለማቀጣጠል በማሰብ ሕጉን መቃመው ከተሰማ ቆይቷል፡፡ አሜሪካ ይህንን ጉዳይ ለተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ለማሳወቅ እሰራለሁ ብትልም ሩሲያ ግን ጉዳዩ የቻይና የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ሌላ የውጭ አካል በጉዳዩ ዙሪያ አይመለከተውም ማለቷ ይታወሳል፡፡ አውሮፓ ሕብረት መሪዎችም በሆንክ ኮንግ ጉዳይ እጅግ እያሰብን ነው ብለዋል፡፡ ይሁንና የሕብረቱ አመራሮች አዲሱ የጸጥታ ሕግ በጣም ያሳስበናል ከማለት ባለፈ ለምን እንዳሳሰባቸው ያነሱት ምክንያት የለም፡፡