“በአየርንብረት ለውጥ አስቸኳይ ጊዜ ወቅት ላይ ነን”-የተመድ ዋና ጸኃፊ
ከሰባት ሀገራት ከተውጣጡ ሰባት ወጣቶች ጋር ቁጭ ብለው እንደሚነጋገሩ ኃላፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተናግረዋል
የተመድ ዋና ጸኃፊ የአየርንብረት ለውጥ ተሟጋቾችን አግኝተው ሊነጋገሩ መሆኑን ገለጹ
የተመድ ዋና ጸኃፊ የአየርንብረት ለውጥ ተሟጋቾችን አግኝተው ሊነጋገሩ መሆኑን ገለጹ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸኃፊ በትናንትናው እለት እንደተናገሩት ስለአየርንብረት የሚሟገቱ ወጣቶችን መደበኛ በሆነ መልኩ ለማግኘት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ኃላፊው የአየርንብረት ለውጥን በመከላከል የተሰማሩትን ወጣቶች ማግኘት የአለም የሙቀት መጠን ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል፡፡
እድሜያቸው18 እስከ 28 የሆኑ ከሰባት ሀገራት ከተውጣጡ ሰባት ወጣቶች ጋር ቁጭ ብለው እንደሚነጋገሩ የተመድ ኃላፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
“የአየርንብረት ለውጥን ለመከላከል የተሰለፉ ወጣት ሰዎችን እያየን ነው፤ ቆራጥ አመራር ምን መሆን እንዳለበት እያሳዩን ነው” ብለዋል አንቶኒዮ ጉተሬዝ፡፡
የወጣቶች አማካሪ ቡድን የተለየ ሀሳብ ለማግኘት ያስችላል፤የአየርንብረት ለውጥን ለመታገል እንደሚያስችል ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
ኃላፊው አሁን ያለነው በአየርንብረትነ አስቸኳይ ጊዜ ወቅት ነው፤ ለቅንጦት የሚሆን ጊዜ የለንም” ብለዋል፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በመልእክታቸውወ ወጣቶች የአየርንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡ወጣት የአየርንብረት ለውጥ ተሟጋቾች በባለፈው አመት መጨረሻ አካባቢ በአየርንብረት ለውጥ ዙሪያ አለምአቀፍ ጫና እንዲፈጠር ለማድረግ የተመድ ኃላፊዎችን አግኝተው ነበር፡፡
በአንድ ቀን የአየርንብረት ለውጥ ስብሰባ በአንድ ቀን ብቻ ከ120 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ1000 በላይ ወጣት የአየርንብረት ተሟጋቾች ተሳትፈው ነበር፡፡
ጉተሬዝ በተመድ ኃላፊነት በፈረንጆቹ 2017 ከተሾሙ ጀምሮ የአየርንብረት ጉዳይን ቀዳሚ አጀንዳ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡