የሩዋንዳ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ
የግጭቱ መነሻ የሩዋንዳ ብሄራዊ ጦር የዲአርሲን ድንበር ጥሶ መግባቱን ተከትሎ ነው
የሩዋንዳ ጦር አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት የዲአርሲን ድንበር ጥሷል ተብሏል
የሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ፡፡
ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዳስታወቀችው ከሆነ የሩዋንዳ ብሄራዊ ጦር ድንበር ጥሶ በመግባት ጥቃት ተፈጽሞብኛል ብሏል፡፡
የሩዋንዳ ጦር በምስራቃዊ ኮንጎ በኩል እስከ ስድስት ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቆ መግባቱ ከኮንጎ አቻው ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል ሲልቬይን ኢክንጌ የሩዋንዳ ጦር ድንበራችንን አልፎ ተኩሶብናል ብለዋል፡፡የሁለቱ ሀገራት ጦር ወደ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው መሰደድ ጀምረው ነበር፡፡
ይሁንና የሩዋንዳ ጦር በከፈተው ተኩስ እስካሁን የተጎዳ ሰው አለመኖሩን አዛዡ ተናግረዋል፡፡ሮይተርስ ግጭቱን አስመልክቶ ከሩዋንዳ ጦር በኩል ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልጧል::
የኮንጎ ብሄራዊ ጦር ባደረገው የመልሶ ማጥቃት የሩዋንዳ ጦር አካባቢውን ለቆ ወጥቷል ተብሏል፡፡
በሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦር መካከል ተመሳሳይ ግጭቶች የተከሰቱ ሲሆን ህፈወጥ ንግድ፤የአማቲያን ጥቃት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ግልጽ ድንበር አለመካለል ለሁለቱ ሀገራት ጦር መጋጨት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡