ፖለቲካ
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ የ39 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ
በአሁኑ ወቅት ጥቃቱ የተፈጸመበትን አካባቢ የዲአር ኮንጎ ወታደሮች እና ፖሊሶች መቆጣጠራቸው ተጠቁሟል
የጥቃቱ ፈጻሚ አይኤስ የተባለው የሽብር ቡድን እንደሆነ ተገልጿል
በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጽንፈኛው አይ ኤስ ኤስ የሽብር ቡድን አደረሰ በተባለ ጥቃት በትንሹ የ39 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
የሽብር ጥቃቱ የተፈጸመው በማዕድን ሀብት በበለጸገችው በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ዲአር ኮንጎ ኪቩ እና ቡጋ በተሰኙ ሁለት መንደሮች እንደሆነ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።
የአደጋው ሰለባዎች በኡጋንዳ የሚንቀሳቀስ አማጺ ቡድን ጥቃቶችን ለማምለጥ በመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው የነበሩ ዜጎች እንደሆኑም ዘገባው አክሏል።
በሀገሪቱ ያለ አንድ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ተቋም ከፍተኛ ሃላፊ ግን ጥቃቱን በኡጋንዳ የሚንቀሳቀሰው የተባበሩት ዲሞክራሲ ሀይል የተሰኘው ጽንፈኛ ቡድን ፈጽሟል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ለዚሁ የዜና ተቋም መናገራቸው ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት ጥቃቱ የተፈጸመበትን አካባቢ የዲአር ኮንጎ ወታደሮች እና ፖሊሶች መቆጣጠራቸው ተጠቁሟል፡፡