“የጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ መታሰር አደገኛ ነው”- መሬም አል ሳዲቅ፣ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
በሱዳን በሲቪል አስተዳደሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት በመካሄድ ላይ ይገኛል
መሬም አል ሳዲቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ገልጸዋል
የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ መታሰር አደገኛ መሆኑን የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሬም አል ሳዲቅ ተናገሩ፡፡
በሱዳን በሲቪል አስተዳድሩ ላይ መፈንቅለ መንግስት የተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክን ጨምሮ በርካታ የሲቪል አስተዳድሩ አመራሮች በእስር ላይ ናቸው፡፡
“በቁም እስር ላይ ናቸው” የተባሉት የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ወደማይታወቅ ቦታ መወሰዳቸው እየተነገረ ነው
ይህን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ መሬም አል ሳዲቅ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ መታሰር “አደገኛ” መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እንዳላወሯቸው ገልጸው ከቃል አቀባያቸው ጋር ስለ ጉዳዩ ማውራታቸውን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ሰምቻለሁ ያሉም ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የሱዳናውያን አብዮት ወኪል” መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የሚደረጉ እንግልቶች እና ጉዳቶች በሱዳናዊያን ላይ ብዙ ጉዳቶችን ያደርሳል ብለዋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ፡፡
“የሱዳን ሽግግር መንግስትን በኃይል መቀየር የአሜሪካን ድጋፍ ያሳጣል”- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ
መሬም ከሰሞኑ በሱዳን ጉብኝት ላይ ካሉት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ ጄፍሪ ፌልት ማን ጋር በሽግግሩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡