ፌስቡክ በሱዳን የሚገኙ ፌክ አካውንቶችን መዝጋቱ አስታወቀ
ፌስቡክ በሱዳን የተዘጉ ፌክ አካውንቶች በስልጣን ሽኩቻ ከተጠመዱት የወታደራዊ እና ሲቪል ክንፎችን ግንኙነት ያላቸው ናቸው ብሏል
ፌስቡክ እስካሁን በሱዳን ከ1.8 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያልዋቸው ከ100 በላይ ፌክ አካውንቶች መዝጋቱንም ነው ያስታወቀው
ፌስቡክ በሱዳን የሚገኙ ፌክ አካውንቶችን መዝጋቱ አስታወቀ፡፡
ፌስቡክ ከቅርብ ወራት ወዲህ በሱዳን የሚገኙ ፌክ አካውንቶች የዘጋበት ምክንያት በሀገሪቱ የሲቪሎች እና ወታደራዊ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን የሰልጣን ሽኩቻ መሰረት በማድረግ አሉታዊ ሚና አላቸው በሚል እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በፌስቡክ የሚሰነዘሩ የህዝብ አስታየቶችና የሚንሸራሸሩ ሀሳቦች ሱዳንን ለ30 ዓመታት ሲገዙ የቆዩትን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን እንደፈረንጆቹ 2019 ከወንበራቸው በማስወገድ በአፍሪካ ቀንዷ ሀገረ ሱዳን አዲስ የዴሞክራሲ ጭላንጭል እንደሚጣ ያስቻሉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
- የሱዳን መንግስትን የሚቃወሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገሪቱ ዜጎች ካርቱም አደባባይ ወጡ
- የቤጃ ጎሳዎች ፖርት ሱዳንን መዝጋታቸውን ተከትሎ በካርቱም የነዳጅ እና የዳቦ እጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በሱዳን የተከፈቱ ፌክ አካውንቶች የሀገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ይበልጥ እንዲጋጋል በማድረግ ላይ በመሆናቸው ያልተረጋገጡና ከወታደራዊው ክንፍ እንዲሁም ከሲቪል አመራሩ ድጋፍ ጋር የሚገኛኙ ናቸው ያላቸውን ገጾች ማገዱ ፌስቡክ አስታውቋል፡፡
በዚህ ሳምንት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ወታደራዊው ክንፍ የካቢኔ ለውጥ እንዲያደርግ በመጠየቅ ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውጭ የመሰባሰባቸው ሚስጥር የፌክ አካውነቶች ውጤት እንደሆነም ነው የተጠቆመው፡፡
ፌስቡክ “በዚህ ወር መጀመርያ ላይ ከወታደራዊ ክንፉ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል 1.1 ሚልዮን ተከታዮች ያሉዋቸው 1 ሺህ የሚጠጉ አካውንት ገጾች እና አውታረ መረቦች ዘግቻለው” ብሏል፡፡
ፌስቡክ የዘጋቸው ገጾች በዋናነት ባላቸው የፖለቲካ እስቤ በሱዳናውያን ዘንዳ በሚፈሩትና የገዥው ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑት ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ/ሄምዲቲ/ የሚመሩ ናቸውም ነው ያለው፡፡
ጀነራል ሄምዲቲ ግን የሱዳን ሽግግር ሂደት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲሳለጥ ከማድረግ በዘለለ ለድጋፍ የማንቀሳቅሳቸው ግለሰቦች የሉም በማለት ወቀሳውን ውድቅ ሲያደርጉ ተደምጠዋል፡፡
ኩባንያው ከወታደራዊ ክንፉ ግንኙነት አላቸው ካላቸው ባሻገር የአል-በሽር ታማኝ ናቸው ያላቸው ፌክ የፌስቡክ አካውነቶችም ዘግቻለው ብሏል፡፡
የፌስቡክ የስጋት መቋረጥ ዳይሬክተር ዴቪድ አግራኖቪች “የግለሰቦቹ ግንኙነት በውስጥ በተደረገ ምርመራ ለማወቅ የተቻለ መሆኑ”ን ተናግሯል፡፡
እሰካሁን በሱዳን ከ1.8 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያልዋቸው ከ100 በላይ ፌክ አካውንቶች ተዘግተዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ ፌክ አካውንትን በመክፈት በመሰል ተግባራት በሚሰማሩ ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስጠንቅቋል፡፡